በደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር የነፋስ መውጫ ፖ/ቴ/ ኮሌጅ ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ሎት1. የፅህፈት መሳሪያ፣ ሎት2. ሕንፃ መሳሪያ፣ ሎት 3. ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት4. የግብርና እቃዎች ፣ሎት5. የሆቴል ማሰልጠኛ እቃዎች ሎት6. ሶስት ኩንታል የሚመዝን የብር ማስቀመጫ ካዝና፣ ሎት7. ጣዉላ እና ተዛማጅ ነገሮች፣ ሎት8. ብረታ ብረት፣ ሎት9. ጨርቃ ጨርቅ፣ ሎት 10. የቤት እና የቢሮ እቃዎች፣ ሎት11. አዉቶሞቲቭ፣ ሎት12. ሸቀጣሸቀጥ፣ ሎት13. መስታወት፣ ሎት 14. የስፖርት አልባሳት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- ህጋዊ ንግድ ፈቃድና ቲን ያላቸው ፎቶ ኮፒውን ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200‚000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወርቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት መወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸዉ፤ ስልክ ቁጥር ጨምሮ የድርጅታቸውን ማህተም መኖር አለበት፡፡
- ጨረታው ከተዘጋጀ በኋላ ተጫራቾች በአቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፤ ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆኑና ለወደፊቱም በመንግስት መ/ቤት በጨረታ የማይሳተፉ ይሆናል፡፡
- ከተጫራቾች ውስጥ አሸናፊ የሆነውን ድርጅት በውሉ መሰረት ነፋስ መዉጫ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ድረስ እቃዉን ማስረከብ አለበት፡፡
- ጨረታው ተከፍቶ እንዳበቃ ከአምስት ቀናት በኋላ ለተከታታይ 5 ቀናት ውል ይሰጣል ፤የውል ማስከበሪያ በመመሪያው መሰረት የዋጋውን 10በመቶ ይሆናል::
- ጨረታው የሚከፈተው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ በ16ኛወ ቀን በ3፡00 ተዘግቶ በ4፡00 ይከፈታል፡፡
- ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15ቀናት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ስለ ጨረታው ሰነድ ማብራሪያ የሚያስፈልጋቸው ከሆነ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት መጠየቅ ይቻላሉ፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ አያስፈልግም ስርዝ ድልዝ ካለው ተቀባይነት የለውም፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ድርጅቱ በውሉ መሰረት እቃዉን ባያቀርብ በውሉ በተመለከተው የገንዘብ መጠን ላይ በየቀኑ 0.1 ወይም 1/1000 መቀጫ እንዲከፍል ይደርግና በዚህ የሚታሰበው የውሉን ዋጋ 10 በመቶ መብለጥ የለበትም፡፡
- ውሉ እንዲፈፀም መዘግየት በስራው እንቅስቃሴ ላይ ተጽእኖ የሚያስከትል ከሆነ የመንግስት መስሪያ ቤቱ የመቀጫው መጠን 10 በመቶ እስኪሞላ ድረስ መጠበቅ ሳይገደድ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውሉን መሰረዝ ይችላል፡፡
- ኮሌጁ በጨረታ ካሸነፈው ተጫራች ላይ 20 በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብት አለው፡፡
- ኮሌጁ አሸናፊውን የሚለየው በነጠላ ዋጋ ነው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50 (ሀምሳ ብር) በመክፈል መዉሰድ ይቻላል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ውል ከወሰዱበት የጊዜ ገደብ ውስጥ እቃውን ባያስገቡ በውሉ መሰረት የሚቀጡ መሆኑን እየገለፅን ለ2ተኛ አሸናፊ የምንሰጥ መሆኑን ወይም ኮሌጁ ለስራ በሚያመቸው መንገድ የምንሰራ መሆኑን ተገንዝበው በተባለው ጊዜ ብቻ እቃውን እንዲያቀርቡ እንገልፃለን፡፡
የነፋስ መውጫ /ፖ/ቴ/ ኮሌጅ

