በማዕ/ጎ/ዞ/በምዕ/ በለሳ ወረዳ የአርባያ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል Susan Thomoson Butfet Foundation በተገኘ በጀት የካርድ ክፍል ግንባታ ፤ ሌሎች የጥገና ስራዎች ፤ የቆሻሻ ማስወገጃ ጉድጓድ ቁፋሮና አሽፒት ፤በአጠቃላይ የቆሻሻ ማስወገጃ የአጥር ግንባታ ለማስገባት በጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው እና
የግባታ ብቃት ደረጃ ከ7 በላይ የሆናችሁ፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
- ተጫራቾች የጨረታ ከወጣበት ከ13/04/2018 ዓ.ም እስከ 27/04/2018 ዓ.ም 11፡30 በተከታታይ ቀናት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላት በሁለት ፖስታ ማህተም ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት በጉልህ ፖስታው ላይ በመፃፍ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የአርባያ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በተዘጋጀው ሳጥን በ28/04/2018 ዓ.ም 3፡30 ድረስ ማስገባት አለባቸው፤ በ3፡30 ታሽጎ በ4፡00 ላይ በግልፅ ይከፈታል ነገር ግን በዚህ ጨረታ የተወዳደራችሁ በአካል ወይም ተወካይ ባይገኙም ጨረታው በሌሉበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ካለው ከፊት ለፊት ልዩ ፊርማዎን ማስቀመጥ ይኖርበዎታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታው ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ ከጠቅላላ የጨረታ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ወይም በጥሬ ገንዘብ የአርባያ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለዕለት ገንዘብ ያዥ ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሰኙን ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ጨረታ ሳጥኑ ከኦርጅናል ሰነድ ጋር ማስገባት አለበት፡፡
- አሸናፊው ተጫራች 30 በመቶ ቅድሚያ ክፍያና 25በመቶ የውል ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ወይም በጥሬ ገንዘብ በባንክ የተረጋገጠ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- ለበለጠ መረጃ ከፈለጉ 09 18 27 70 37 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በሎት ( በጥቅል ዋጋ ) ሲሆን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለፋይናንስ ግምገማ ያለፉት ተጫራቾች በቁጥር ቢያንስ 3 እና ከዚያ በላይ ከሆነ በጨረታ አከፋፈት ወቅት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ የሂሳብ (እርቲሜቲክ ቸክ) ከተሰራ በኋላ የተደረሰበት ልዩነት እስከ 2.5 በመቶ ድረስ ከሆነ ተቀባይነት የሚኖረው ሲሆን ከዚህ የበለጠ ልዩነት ካጋጠመ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
- ለፋይናንስ ግምገማ ያለፉት ተጫራቾች ከቁጥር 3 በታች ከሆነ በጨረታ አከፋፈት ወቅት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ የሂሳብ (እርቲሜቲክ ቸክ) ከተሰራ በኋላ የተደረሰበት ልዩነት እስከ አንድ በመቶ ድረስ ከሆነ ተቀባይነት የሚኖረው ሲሆን ከዚህ የበለጠ ልዩነት ካጋጠመው ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
- ሁሉንም ለዕድሳቱ እና ለግባታው የሚያስፈልጉ የግንባታ ዕቃዎች በተጫራቾች የሚቀርብ ሁኖ ስራውን ይሰራሉ፡፡
- አሸናፊው የሚለየው የብቃት ደረጃቸው ከ7 ጀምሮ ካሉት ዝቅተኛ ዋጋ ባቀረበው አሸናፊውን እንለያለን፡፡
- የሚሰራ የስራ ዝርዝር መግለጫ ( እስፔስፊኬሽን ) ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በማንኛውም ስዓት በአር/የመ/ደረ/ ሆስ/በግ/ፋ/ ቡ/የዕለት ገ/ሰብሳቢ ቢሮ ቁጥር 20 መግዛት ወይም ማግኘት ይችላሉ
- አሸናፊው ድርጅት ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምዕራ/በ/ወ/ ዐ/ህግ ጽ/ቤት ቀርቦ ውል መውሰድ የሚችል መሆን አለበት
ማሳሰቢያ፡- ጠቅላላ የተዘረዘሩት ስራዎች ( ግንባታውን ) በ60 ቀናት ውስጥ አጠናቀው ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
የአርባያ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

