ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
56

በደቡብ /ጎ/አስ/ ዞን በታ/ጋ/ወ/ የዶ/ር አምባቸዉ መኮነን መታሰቢያ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውሉ አቅርቦቶችን ሎት1. የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት2. ህትመቶች፣ ሎት3. ሌሎች አላቂ እቃዎች (የጽዳት እቃዎች)፣ ሎት4. ለህንጻ፣ለቁሳቁስና ለተገጣጣሚዎች እድሳትና ጥገና፣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ተቋሙን ማሳደስ ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ግብር ከፋይ መለያ (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. የግዥዉ መጠን ከ200,000.00 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት  መቅረብ የሚችሉ
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን አቅርቦት ዓይነቶች ዝርዝር መገለጫ (እስፔፍኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የእያንዳንዱን ሎት በማይመለስ00 (አንድ መቶ ብር) ከእለት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 11 በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የእቃዎን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሰ.ፒኦ) ወይም በሁኒታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ  ገንዘብ  ማስያዝ በዶ/ር አምባቸዉ መኮነን መታሰቢያ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ህጋዊ ደረሰኝ መሂ1 ተቆርጦ ኮፒዉን ወይም የጥቃቅን ልዩ ድጋፍ ከሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸዉ፡፡
  9. ሎት4 ላይ የተጠቀሰዉ ለህንጻ፣ ለቁሳቁስና ለተገጣጣሚዎች እድሳትና ጥገና ተጫራቾች ሙሉ እቃዉን ራሳቸዉ በማቅረብ መስራት የሚችሉ መሆን አለባቸዉ፡፡
  10. ጨረታው በጋዜጣዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ  ለ15ተከታታይ ቀናት ማንኛውም ተጫራች የጨረታ  ሀሳቡን በአንድ ወጥ በሆነ ፖስታወች  የድርጅቱን  ክብ ማህተም በመምታት በጥንቃቄ በማሸግ በግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሬ ቄጥር 7 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን  ወይም በ16ኛዉ ቀን 4፡00 ድረስ በሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው  በተገኙበት /ባይገኙም/ በ16ኛው በ4፡00 ሰአት ላይ ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ይከፈታል ፡፡ ሆኖም ግን ተጫራቶች  በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት  ጊዜ ባይገኙም ጨረታውን መከፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታ ሂደቱ ለሚተላለፍ ውሳኔወች ተገዥ ይሆናል፡፡
  12. አንድ ተጫራች በአንድ ሎት ዉሥጥ የተዘረዘሩትን የአቅርቦት አይነቶች አካተዉ መሙላት አለባቸው፡፡
  13. በእያንዳንዱ ምድብ አሸናፊ የሚሆነዉ መስፈርቱን በማሟላት ከጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ የሞላዉ ነው፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. መ/ቤቱ እንደ በጀቱ አቅም 20በመቶ የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. አሸናፊዉ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 የስራ ቀናት በኋላ  ባሉት 5 የስራ ቀናት ዉስጥ የዉል ማስከበርያ 10በመቶ በማስያዝ በባንክ በተረጋገጠ  ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ዉል መፈጸም ይኖርበታል፡፡ በተባለዉ ቀን ዉል መፈጸም ከልቻለ የጨረታ ማስያዣዉ ለመ/ቤቱ ገቢ ይደረግበታል፡፡
  17. አሸናፊዉ ድርጅት ወይም ግለሰብ ዉል ከፈጸመ በኋላ ያሸነፋቸዉን እቃዎች ዶ/ር/ አምባቸዉ መኮነን መታሰቢያ የመጀመበሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድረስ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ  ጥራቱን በማሳየት ለንብረት ክፍል ያስረክባል፡፡
  18. በዚህ ሰነድ ያልተገለጸ ሃሳብ ቢኖር በግዥ መመሪያዉ መሰረት ተግባራዊ ይሆናል፡፡
  19. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ የዶ/ር አምባቸዉ መኮነን መታሰቢያ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 268 03 10 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የዶ/ር አምባቸዉ መኮነን መታሰቢያ የመጀመሪያ ደ/ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here