ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
112

የደቡብ ጎንደር ዞን የደራ ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት 1ኛ.ለደራ ወረዳ መንገድ እና ትራንስፖርት ጽ/ቤት ጉሀ ቀበሌ ከጎሽዱር እስከ ደንበዛ ማእከል ድረስ 8.265 ኪ.ሜ እንደኛ ደረጃ የገጠር መንገድ፣ 2ኛ. ለደራ ወረዳ መሬት ጽ/ቤት ለግብርና ፑል ላሉ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ፤የቢሮ ግንባታ የእጅ ዋጋ በመደበኛ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ስራ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. የሙያ ብቃት ያላቸው እና ከአሁን በፊት መንገድ ስራ ሰርተው የመልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. በዘመኑ የታደሰና በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  3. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ለጠቅላላ ስራ ተቋራጭ እና ለመንገድ ስራ ተቋራጭ ደረጃ አምስት እና ከዚያ በላይ የሆኑ፡፡
  6. የቢሮ ግንባታ የህንፃ ስራ ተቋራጭ ደረጃ ስድስት እና ከዚያ በላይ የሆኑ፡፡
  7. ግዠው ከ200‚000 (ሁለት መቶ ሽህ) ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  8. ከተራ ቁጥር 1-7 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  9. ተጫራቾች በድርጅታቸው ስም የተቀረፀ ማህተም ሊኖራቸው ይገባል፡፡
  10.  የስራው አይነትና ዝርዝር መግለጫ ወይም ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100 (አንድ መቶ) ብር በመክፈል ደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  12.  ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የስራ አይነት ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በጽ/ቤቱ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ማስያዝ አለባቸው፡
  13. የገዙትን የጨረታ ሰነድ ዋጋ በመሙላት እና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ በተለያየ ፖስታ ኦርጅናሉን እና ኮፒ በማሸግ ከፖስታው ጀርባ ለደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በማለት ስምና የሚወዳደሩበትን አይነት በመግለጽ ዘወትር በስራ ሰአት በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  14.  የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 21 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ፤ በ22ኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ ከቀኑ 4፡00 ታሽጐ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡ 22ኛው ቀን በአል ቀን ከሆነ በቀጣዩ ስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  15. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር ሁኔታ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 258 041 ወይም ቢሮ ቁጥር 2 በአካል በመገኘት መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የደራ ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here