ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
43

ቁጥር-001/2018

በአብክመ የግብርና ቢሮ የሰሜን ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ የግብዓት ገጠር ፋይናንስ አቅርቦት ቡድን ለ2018/2019 የምርት ዘመን አገልግሎት የሚውል የዳፕ እና ዩሪያ በድምሩ 1,220,000 (አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃያ ሺህ ) ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በመርከብ ዩኒየን በስሩ ባሉ 75 መሠረታዊ ማኅበራት መጋዘን ድረስ ለማጓጓዘ ብቃት ያላቸውን የትራንስፖርት ደርጅቶች በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ውል ከተፈፀመበት ቀን  እስከ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ የሚቆይ የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል። የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር (ገበያ ልማት ሚኒስቴር) ቢሮ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና የዘመኑ የመንግስት ግብር ለመክፈላቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፡፡ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት/ቲን/ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. በጨረታው የሚሣተፉ ተጫራቾች ከ70 ኩንታል በላይ የሚጭኑ ተሽከሪካሪዎች የሚያቀርቡ ከሆነ ከፌደራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ተመዝግበው የተደራጁ ሆነው በዘመኑ የታደሠ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ከ70 ኩንታል በታች ከሆነ በክልል ትራንስፖርት ቢሮ ተመዝግበው የተደራጁ ሆነው በዘመኑ የታደሠ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ
  4. የተሽከርካሪ ዝርዝር ተ.ቁ ፣የሴሌዳ ቁጥር፣ የመኪናው ዓይነትና የመጫን አቅም የሚያስረዳ ከፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ወይም ከክልል መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ የተሰጠ የ2018 ዓ.ም ወቅታዊ የታደሠ ምዝገባ ፊቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ 1 እስከ 4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚጓጓዘውን የአፈር ማዳበሪያ አይነት፣ መጠን ርቀት በኪሎ ሜትር ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል ሰ/ጎጃ/ዞ/ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 8 ማግኘት ይቻላል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታዎች ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (ኦሪጅናል) በሚወዳደሩበት መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ ማህበራት ዩኒየን ስም ማስያዝ አለባቸው።
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሠነዱን በአንድ ፖስታ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በማሸግ በአብክመ ግብርና ቢሮ የሰሜን ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ በግብርና ግብአት ገጠር ፋይናንሰ አቅ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 303 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው በበኩር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ማለትም 4፡00 ብቻ ሠነዱን በሳጥኑ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 4፡01 የጨረታ ሳጥኑ ይጣሸጋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈተው በእለቱ  4፡30  በመምሪያዉ  በሚዘጋጅ ቦታ ይከፈታል ፡፡
  10. መምሪያዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ መምሪያዉ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 12 76 42 43/09 23 89 92 89 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

የሰሜን ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here