ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
79

የጨረታ ቁጥር፡-003/2018

የአብክመ ውሀና ኢነርጂ እና የማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ በመደበኛ እና በተለያዩ ፕሮግራም በጀት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ሎት1. የቢሮ መገልገያ እቃዎች (ኤሌክትሮኒክ) ላፕቶፕ ፣ዴስክ ቶፕ ፣ፕሪንተር ፣AC ወዘተ ሎት2. ብስክሌትና የብስክሌት ጎማ ሎት3. የተሽከርካሪ መለዋወጫና fast moving እቃዎች ፣ ሎት4. ዘይትና ቅባት፣ ሎት5. የጽህፈት መሳሪያ ፣  ሎት 6.የጽዳት እቃ፣ ሎት7. ጎማና ባትሪ ሎት8. ፈርኒቸር፣ ሎት9. ጋዜጣና መጽሄት አመታዊ ውል፣ ሎት10.የግቢ ጽዳት አመታዊ ውል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
  2. የግዥው መጠን በየንግድ ዘርፉ 200,000 (ሁለት መቶ) ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ሎት 1.  50,000 (አምሳ   ሽህ )፣ ሎት 2.እና ሎት 3. 3,000 ( ሶስት  ሽህ )፣ ሎት 4.10,000 (አስር ሽህ)፣ ለሎት 5. 3,000 (ሶስት ሽህ )፣ ለሎት 6. 2,000 (ሁለት ሽህ )ሎት7. 20,000 (ሀያ ሽህ)፣ ሎት8. 2,000 (ሁለት ሽህ)፣ሎት9. 3,000 (ሶስት ሽህ ) ሎት10.5,000 (አምስት ሽህ)  በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. በጨረታው ፍላጎት ያላቸው ህጋዊ ድርጅቶች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ ቢሮ ቁጥር 23 በመቅረብ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር  100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚቻል ሲሆን ተጫራቾች ለመወዳደር የመወዳደሪያ ሰነዶችን ሲመልሱ የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማ እና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  7. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን  8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ይከፈታል፡፡ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ውሀና ኢነርጂ ቢሮ  ይከፈታል ፡፡
  8. ተጫራቾች ከአሁን በፊት የመንግስት ግዥዎች ላይ ተሳትፈው አሸናፊ መሆናቸው ተገልፆላቸው ቀርበው ውል ለመያዝ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወይም ውል ይዘው በአግባቡ ባለመፈፀማቸው እርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም የተወሰደው እርምጃ በማስረጃ የተደገፈ መሆን አለበት፡፡
  9. የማቅረቢያ ጊዜ ውል ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ15 ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ርክክብ የሚፈፅም ይሆናል፡፡ ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ  ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 058 222 01 32/058 220 10 87 ዘወትር በስራ ቀናት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  12. አድራሻ የአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ ቀበሌ 07 ባህር ዳር ዩንቨርስቲ ዊዝደም ፊት ለፊት

የአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here