ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
147

የቢቡኝ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት በብ/የሚ/የግ/ግ ክ/ቡድን በ2016 በጀት ዓመት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የአፕል መሰረተ ግንድ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የብቃት ማረጋገጫ ስርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የግብር ከፋይ መለያ (ቲን) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  3. ተወዳዳሪዎች የአፕል መሰረተ ግንዱ ማቅረብ የሚችሉ በክልሉ ውስጥ ብቻ መሆን አለበት፡፡
  4. የአፕል መሰረተ ግንዱ የችግኝ ቁመት ከ1.3 ሜትር ቁመት ያለው እና የተስተካከለ፣ ችግኙ በሁሉም አቅጣጫ ሥር ያለው፣ ከበሽታ እና ከተባይ ነፃ የሆነ፣  ከኳራንታይን የጥራት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል እና ዝርያውን ሊገልፅ የሚችል፣ የችግኝ ውፍረት ከእርሳስ ቅርፅ ያላነሰ ወይም ያልወፈረ መሆን አለበት፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ፣ የአሠሪው መስሪያ ቤት እና የተጫራቹ  ሙሉ ስም፣ አድራሻ፣ ፊርማ እና ማህተም በማስቀመጥ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚገዛ የአፕል መሰረተ ግንድ አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት 30.00 /ሰላሳ ብር/ የማይመለስ በመክፈል ከቢ/ወ/ገ/ኢ/ል/ፅ/ቤት ደ/ሂ/ደ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢ/ወ/ግ/ፅ/ቤት/በብ/የሚ/የግ/ግ/ክ ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ19/09/2016 ዓ.ም እስከ 07/10/2016 ዓ.ም 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በዚሁ ቀን 11:30 ላይ ይታሸጋል፡፡
  10. ጨረታውን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግብ/ፅ/ቤት/በብ/የሚ/የግ/ግ/ክ ቡድን በቢሮ ቁጥር 06 በ08/10/2016 ዓ.ም በ 3፡00 ይከፈታል፡፡
  11. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ በተገለፀበት በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ ይኖርበታል፡፡
  12. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ሃያ በመቶ የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን በሚከፍትበት ቀን ብሄራዊ በዓል፣ ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  14. አሸናፊው ድርጅት የተጠየቁ ግብዓቶችን በሙሉ ቢ/ወረዳ ፋሲለደስ ችግኝ ጣቢያ በሙያተኛ ተረጋግጦ ገቢ ይደረጋል፡፡
  15. ሰለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 06 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 254 06 04 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የቢቡኝ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here