ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
204

በአበከመ ገንዘብ ቢሮ  በሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር የደባርቅ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ዋና ጽ/ቤት በስሙ ለተመዘገበው የመኖሪያ ቤትና ቦታ አድራሻ ደባርቅ ከተማ ቀበሌ 03 ልዩ ቦታው መድሐኒዓለም ሰፈር በእዳ ተረክቦ በስሙ ያስመዘገበውን ቤት  በአዋሳኝ  በምሥራቅ  ቢራራ ታደሰ፣ በምዕራብ አህመድ አሊ፣ በደቡብ አስማማው ሃይሉ እና በሰሜን መንገድ የሚያዋስነውን 250 /ሁለት መቶ ሃምሳ/ ካሬ ሜትር ቤትና ቦታ   በግልፅ  ጨረታ  አወዳድሮ  መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ተወዳዳሪዎች  ሊያሟሉት የሚገባቸው፡-

  1. ማንኛውም ሰው የጨረታ ሰነዱን ገዝቶ መወዳዳር ይችላል፡፡
  2. ተወዳዳሪዎች ለሚወዳዳሩበት የቤት ጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ  ብር/ በመክፈል  ደባርቅ ወረዳ ገንዘብ  ጽ/ቤት ከፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  3. ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ  ወይም /ሲ.ፒ.ኦ/ በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1  ጨረታው እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ ለግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ውስጥ ወይም  ከኦርጅናል ጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ በማሸግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይሁን እንጅ የጨረታ ማስከበሪያ ጥሬ ገንዘብ ፖስታ ውስጥ  ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አይፈቀድም፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይም ያስያዙት ሲፒኦ (ጥሬ ገንዘብ) ከሁለት በመቶ ቢያንስ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተወዳዳሪዎች  ከውድድሩ ውጭ ይሆናሉ፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ሲሞሎ ሥርዝ ድልዝ ካለው በራሳቸው ፊርማ ፓራፍ በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ  በደባርቅ ዙርያ ወረዳ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን  ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ስዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  5. አሸናፊ ግለሰብ አሸናፊነቱ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ በ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ሙሉ ክፍያ ከፍሎ ስመ-ንብረት ዝውውር  ማዛወር አለበት፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ በተቀመጠለት ጊዜ ገደብ ያሸነፉበትን ገንዘብ ባይከፍል  ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ የሚወረስ ይሆናል፡፡
  6. ጨረታው በአየር ላይ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ በበኩር ጋዜጣ ዕትም ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት ወይም ከ09/07/2016 እስከ 29/07/2016 ይሆናል፡፡
  7. ጨረታው በጋዜጣ በወጣ በ22 ተኛው ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን ይህ ቀን በበዓል /በካላንደር/ ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የመንግሥት የሥራ ቀን ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 በግልጽ ይከፈታል፡፡
  8. ተወዳዳሪዎች ለሚወዳደሩበት የቤትና ቦታ ጨረታ በቀን  ከ20/07/2016 እስከ 27/07/2016 በጽ/ቤቱ በኩል  በአካል ቀርበው  መጎብኘት ይችላሉ፡፡
  9. ተወዳዳሪዎች በሚያቀርቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው፡፡
  10. ተወዳዳሪዎች ሚወዳዳሩበት የቤት እና የቦታ መነሻ ዋጋ 1,900,000 /አንድ ሚሊዮን ዘጠኝ  መቶ ሺህ ብር/ ሲሆን  ከመነሻ ዋጋ  በታች የሚሞላ ተወዳዳሪ ውድቅ ይሆናል፡፡
  11. ተወዳዳሪዎች አሸናፊ ሁነው የሚመረጡት ከተወዳዳሪዎች ውስጥ ከፍተኛ ዋጋ የሞላው ይሆናል፡፡
  12. የጨረታ መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና እራሳቻውን ማግለል አይችሉም፡፡
  13. መሥሪያ ቤቱ ይሄን  ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ  በከፊልም ሆነ ሙሉ  በሙሉ  የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ስለጨረታ ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው በሥራ ሂደቱ  ቢሮ ቁጥር 3 ዘወትር በሥራ ሰዓት በአካል ቀርበው ወይም በስልክ ቁጥር 058 117 00 11 ወይም 09 18 43 91 36 ደውለው  መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የደባርቅ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here