በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የባሕር ዳር ከተማ አስ/ከተማ እና መሰረተ ልማት መምሪያ በ2016 በጀት ዓመቱ የፓምፕ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር እንደምትችሉ እንገልጻለን፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- ግብር ከፋይ መለያ (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥ መጠኑ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የተጫራቾች የጨረታ ማስከሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 198,000.00 (አንድ መቶ ዘጠና ስምት ሺህ ብር) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በነጠላ ዋጋ ነው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሱቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ማለትም ኦርጅናል እና ኮፒ ተለይቶ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ /ንብ/አስ/ ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 205 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ከ2፡30 እስከ 15ኛው ቀን 11፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ን/አስ ቡድን ክፍል በቢሮ ቁጥር 205 በ15ኛው ቀን በ11፡00 ታሽጎ በ16ኛው ቀን በ3፡30 ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ከሥራ ቀናት ውጭ ከሆነ ወደሚቀጥለው የሥራ ቀን ይዛወራል፡፡
- ጨረታው ሁለት የግምገማ ሂደቶች ይኖሩታል፡፡ የመጀመሪያው ሂደት /ደረጃ የቴክኒካል ሰነዶች ግምገማ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ቴክኒካል ግምገማውን ካለፉት ተጫራቾች ውስጥ የአማራ ብሔራዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ በቁጥር አብክመ ገ/ቢ/ኮቢ01/02 በቀን 15/09/2014 ዓ.ም በተሻሻለው መመሪያ መሰረት የጨረታ ዋጋ ያቀረበውን ተጫራች መምረጥ ይሆናል፡፡ ለበለጠ መረጃ ይህን መመሪያ በደንብ ያንብቡት፡፡
- የፓምፕ ግዥ አሸናፊ ለምትሆኑ ተጫራቾች ግዥው የሚፈጸመው መሥሪያ ቤቱ /ግዥ ፈፃሚው በሚያቀርበው ናሙና ላይ የተመሰረተ ይሆናል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 205 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 18 78 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚፈልጉ ማንኛውም ሕጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ 1,500.00 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የፓምፕ ግዥ ሥራ ወጭዎችን የሚሽፍነው አሸናፊ ተጫራች ይሆናል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በክፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የባሕር ዳር ከተማ አስ/ ከተማ እና መሰረተ ልማት መምሪያ