ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
151

የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የጽዳት፣ የጽህፈት እና የመኪና ጌጣጌጥ እቃ ለመግዛት የወጣ ግልጽ ጨረታ ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የታደሠ የንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ቲን ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ሆነው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና ለእቃው ቀጥተኛ የሆነ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ማለትም ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ በመምጣት ሠነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ በኦርጅናል የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት በፖስታ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው፡፡
  4. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን 17/10/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታ ሠነዱን በመግዛት በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡15 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በጨረታው ከሚቀርቡ አገልግሎት ከጠቅላላ ዋጋ ላይ ሁለት በመቶ በባንክ በተመሠከረለት ቼክ ወይም ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ማንኛውም ዋጋ የሚሞላውና ክፍያ የሚፈፀመው በኢትዮጵያ ብር ብቻ ነው፡፡
  5. በጨረታው የሚሳተፈው ተወካይ ከሆነ ሕጋዊ የሆነ ውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፤ ተጫራቾች በወቅቱ አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
  6. በጨረታው አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ ተገልጾለት ውል ከወሰዱበት ቀን ጅምሮ በ3 ቀናት ውስጥ እቃውን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  7. በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ቢፈልጉ በስልክ ቁጥር 058 218 03 41 /058 218 11 94 መጠየቅ ይቻላል፡፡
  8. ተጫራቾች ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን ማቅረብ አለባቸው፡፡
  9. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here