ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
121

የፍ/ሰላም ከተማ አስተዳደር ወጀት ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለመንገድ ሥራ አገልግሎት የሚውል ስሚንቶ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፣

  1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስራጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. የተሞላው ዋጋ ማንኛውንም ግብር ወይም ታክስ ያካተተ መሆን አለበት፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያና ዋስትና ለሚወዳድሩበት ብር ወይም ዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲ.ፒ.ኦ ወይም ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የዋጋ መሙያ ሰነዳቸው ላይ ማህተምና ፊርማ በማድረግ በፖስታ በማሸግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት በአስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ደጋፊ የሥራ ሂደት ጨረታው ከወጣበት ቀን ለአስር ተከታታይ የሥራ ቀናት በአየር ላይ ይውልና በአስራ አንደኛው ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፣ ባይገኙም ጨረታውን ለመክፈት አያስተጓጉልም፡፡
  11. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09 13 75 77 87 /058 775 22 54 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  13. ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ የተጫረቱትን የግንባታ ቁሳቁስ አጓጉዘው ፍ/ሰላም ከተማ መሥሪያ ቤቱ ያዘጋጀው ቦታ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  14. ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ የተጫረቱትን የግንባታ ቁሳቁስ አጓጉዘው በፍጥነት ማቅረብ መቻል አለባቸው፡፡
  15. ከላይ ስለ ጨረታው ያልተገለጹ ነገሮች ቢኖሩ በ2003 የግዥ አፈፃፀም መመሪያ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡

ወጀት ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here