ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
131

የጨረታ ቁጥር 007/2016

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የውሃ እና  ኢነርጅ  ቢሮ በመደበኛና ከተለያዩ ፕሮጀክቶች በተገኘ በጀት የሦስተኛ ወገን  የመድን ሽፋን   ዓመታዊ ውል  ተወዳዳሪዎችን  አወዳድሮ መግዛት  ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ሁሉ እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡-

  1. በዘርፉየታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው እና የግዥው መጠን ከ200‚000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. የኢንሹራንሹ  ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታሰነዱማግኘትይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ00 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የውሃ እና  ኢነርጅ ልማት ቢሮ ቁጥር 23 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ 40,000 /አርባ  ሺህ ብር/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በውሃ እና ኢነርጅ ቢሮ ቢሮ ቁጥር 27 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ የመቁጠሪያ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
  9. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በመሙላት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ 16ኛው ቀን 8፡00 ከመድረሱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ቀን 8፡00 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 27 በ8፡30 ይከፈታል፡፡
  10. የጨረታ መዝጊያ ቀን /16ኛው ቀን/ በዓል ቀን ከሆነ በተመሳሳይ ሰዓት በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  11. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  12. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 058 222 01 32 /058 220 10 78 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የአብክመ ውሀ እና ኢነርጅ  ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here