ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
130

የመቄት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለመቄት ወረዳ እንስሳት ሃብት ልማት ተጠሪ ጽ/ቤት በተዘዋዋሪ ፈንድ በጀት ለእንስሳት ህክምና አገልግሎት የሚውል መድኃኒት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. የቲን ነምበር ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  2. ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  3. የሙያ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  4. ግዥው ከ200,000.00 /ከሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  5. የጨረታ ማስከበሪያ አንድ በመቶ 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ ብቻ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ማስያዝ የሚችሉ፡፡
  6. የውል ማስከበሪያ አስር በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ማስያዝ የሚችሉ፡፡
  7. በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ የሌለው፡፡
  8. የጨረታ መክፈቻ ቀን ካላንደር ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ ቀጣይ ባሉት የሥራ ቀናት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱን ኮፒና ኦርጅናል በመለየት በታሸገ ፖስታ ማስገባት የሚችል፤ ኮፒ ባለማድረጉ ጨረታውን ውድቅ አያደርገውም::
  10. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ከ24/10/2016 ዓ.ም እስከ 8/11/2016 ዓ.ም ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ 11፡30 የጨረታ ሰነዱ ይሸጣል፡፡
  11. ጨረታው የሚከፈተው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ09/11/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ የሚከፈት ይሆናል፡፡ ሰለዚህ መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን መ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት/ግ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 13 በመቅረብ የማመለስ 100.00 /አንድ በመቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት ትችላላችሁ፡፡ መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  • የጨረታ ሰነዱ የሚገባው ግ/ን/አ/ደ/የስ/ሂደት ቢ.ቁ. 13 በሚገኘው ሳጥን ውስጥ ነው፡፡
  • ለበለጠ መረጃ በዚህ ስልክ ቁጥር 033 211 00 91 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የመቄት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here