የደብረ ማርቆስ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ2017 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ የሠራተኞች የሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጥ 60 እና ከዚያ በላይ ወንበር ያለው 1ኛ ደረጃ አውቶቢስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- ግዥው ከ200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ጨረታ ማስከበሪያ 3,000.00 /ሦስት ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ኦርጅናሉን ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ የደረሰኞችን ፎቶ ኮፒ ከፋይናንስ ወይም ከዋጋ ማቅረቢያ ፖስታ ውስጥ አስገብቶ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀን በአየር ላይ ቆይቶ በ16 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 8፡00 ይከፈታል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡
- የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አ/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ ዋጋው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን አንስቶ የሚቆጠር ዝቅተኛ ቀን 40 ቀናት ይሆናል፡፡
- የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከግ/ፋ/ን/አ/ደ/የስ/ሂደት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 771 22 46 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡