በአብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ ባሕር ዳር ከተማ የሚገኘው አዲስ ዓለም ሆስፒታል ለተኝቶ ታካሚዎች የምግብ አቅርቦት አገልግሎት የሚውል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መስፈርቱን የሚያሟሉ ሁሉ መሳተፍ ይችላሉ፡፡ መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡-
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ያላቸው፡፡
- ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ከቆየ በኋላ በ16ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 8 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ለተኝቶ ታካሚዎች የምግብ አቅርቦት ጨረታ ዝርዝር መግለጫ ወይም እስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያ /ቢድ ቦንድ / ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሰፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ሀሳቡን በታሸገ ፖስታ በአዲስ ዓለም ሆስፒታል ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 8 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 /በአስራ አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 /በአምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ (መያዣያ) በቁርጥ ዋጋ 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 8 መገኘት ይችላሉ፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው መረጃ ለማግኘት ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 218 10 34 /09 40 90 84 37 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአዲስ ዓለም ሆስፒታል