ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
152

በምዕራብ ጐጃም ዞን የዳሞት የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ. የበቆሎ ዱቄት ቅንጨ እና ሌሎች ምርቶች ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ባንኬብል አዋጭነት ጥናት የሚሠራ ሲሆን  አዋጭነት ጥናቱ ከዚህ በፊት የተሠራና የአማካሪ ቅጥር የተፈፀመ ስለሆነ ጥናቱ አብዴት ተደርጎ ለባንክ የሚቀርብ አዋጭነት ጥናት ማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-

  1. በዘርፍ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና በሙያው ማረጋገጫ ማቀረብ የሚችሉ፡፡
  2. የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
  3. ቢቻል ከዚህ በፊት የተሠሩ አዋጭነት ጥናት ማቅረብ ቢቻል፡፡
  4. ባንኬብል ቢዝነስ ፕላን ለባንኮች የሚቀርብ ስለሆነ ባንኮች በሚሰጡት ግብረ መልስ መሰረት አስተካክሎ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
  5. ሁሉም በጥናቱ መካተት የሚገባችው ዝርዘር ሥራዎች አካቶ መሥራት አለበት፡፡
  6. በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከፋይናንስ ዋጋ ማቅረቢያ ፖስታ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  7. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ 100.00 /አንድ በመቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከዩንየኑ ሂሳብ ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. የጨረታ ሰነዱን በኦርጅናል የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት በድርጅቱ ማህተም በተዘጋጀ ፖስታ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ወይም ማቅረብ አለባቸው፡፡
  9. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለተከታታይ 11 የሥራ ቀናት እስከ ቀኑ 8፡00 አየር ላይ ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን 8፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በ11ኛው ቀን 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያስተጓጎልም፡፡
  10. ጨረታውን ያሽነፈ ተጫራች ጨረታው ተከፈቶ አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ድምር አስር በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ አለበት፡፡ ይህንን ካላደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ሁለት በመቶ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
  11. ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. በዚህ ያልተጠቀሱት ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሠረት የሚሰተናገዱ ይሆናሉ፡፡
  13. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 774  06 40 በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መስተናገድ  ይችላሉ፡፡

የዳሞት የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here