ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
164

የአብክመ ሥራና ሥልጠና ቢሮ ለቢሮአችን ተሸከርካሪ መኪኖች ለ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ለአገልግሎት የሚውሉ ሎት1. የመኪና የመለዋወጫ ዕቃ ፣ ሎት2. የመኪና ጥገና ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ  ዓመታዊ ውል በመያዝ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች ሁሉ በጨረታ ሰነዱ መሠረት መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. የጨረታው አይነት :- የመለዋወጫ ዕቃ ግዥ እና የጥገና ሥራ አገልግሎት፡፡
  2. በጨረታው መሣተፍ የሚችሉ፡-
    1. አግባብነት ያለው ሕጋዊና በዘርፉ የተሰማሩ የሥራ ፈቃድ ያላቸው ሆኖ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ወይም የሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
    2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ ግዥው 200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በመሙላትና አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በፖስታ በማሸግ ቢሮ ቁጥር G001 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች በፖስታ በማሸግ ከጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. በማንኛውም እቃ ግዥ ዋጋ 10,000.00 /አስር ሽህ ብር/ ለአገልግሎት 3000.00/ሦስት ሽህ ብር/ ለሚሆኑ ግዥዎች አቅራቢው ከሚፈፀምለት ክፍያ ላይ ሁለት በመቶ የቅድመ ግብር ክፍያ ተቀንሶ የሚቀር ይሆናል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአብክመ ሥራና ስልጠና ቢሮ፤ ቢሮ ቁጥር 01  00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ከሚያቀርበው ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተመሰከረለት ቼክ /ሲፒኦ/ በደረሰኝ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  8. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የጨረታው ሰነድ ላይ የተሞላውን የዋጋ ማሻሻል፣ መለወጥ ወይም ጨረታውን ሰርዣለሁ የሚሉ ጥያቄዎች ተቀባይነተ የላቸውም፡፡
  9. የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይቆያል፤ በ16ኛው ቀን በ14/12/2016 ዓ.ም 4፡00 ተዘግቶ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሥራና ስልጠና ቢሮ ቁጥር G004 ይከፈታል:: በአስራ ስድስተኛው ቀን  ቅዳሜ፣ እሁድ ወይንም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. ተጫራቾች የግዥውን አይነትና መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  11. ቢሮው ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ /መረጃ/ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 226 53 95 / 058 226 53 97 መጠቀም ይችላሉ፡፡
  13. ቢሮው ለአሠራር ያመቸው ዘንድ ጨረታውን ሎት 1. በተናጥል፣ ሎት 2. ደግሞ በሎት ድምር የሚያወዳድር መሆኑን አውቃችሁ የዋጋ መሙያውን በጥንቃቄ ሞልታችሁ እንድታቀርቡ እንገልጻለን፡፡
  14. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ተሞልቶ፣ ከጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ ጋር ተያይዞ በፖስታ በማሸግ የሞሉትን የግዥ አይነትና የጨረታውን ዘዴ /ግልጽ ጨረታ/ በሚል ተጽፎ መቅረብ አለበት፡፡

የአብክመ ሥራና ሥልጠና ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here