በደቡብ ወሎ ዞን የተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት ለወረዳው መኪኖች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. የመኪና እቃ፣ ሎት 2. የመኪና ጎማ ከነካለማደሪያው በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- ሕጋዊና የታደሰ ንግድ ፈቃድና ቲን ያላቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ከተ.ቁ 1-2 የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውንና ተፈላጊ መረጃዎችን የዋጋ ማቅረቢያ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ በማለት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ በታሸገ ኢንቨሎፕ የመወዳደሪያ ዋጋቸውን ኦርጅናልና ኮፒ በማለት የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ በመሆኑ መሥሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡
- የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በቀጣይ የሥራ ቀን የመክፈቻ ሰዓቱን ጠብቆ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የእቃ አገልግሎት ዝርዝር ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ውስጥ የአንዱ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋውን እንዲሁም ቀን፣ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ጠቅላላ ዋጋ ታክስን የሚያካትት ወይም የማያካትት መሆኑን መግለጽ አለባቸው፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በሎት ድምር ዋጋ ነው፤ በሰነዱ የተዘረዘሩትን እቃዎች ዋጋ በሙሉ ያልሞላ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናል፤ አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ተጫራች መሥሪያ ቤቱ በጠየቀው ስፔስፊኬሽን መሰረት የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የሞሉት ዋጋ ከወቅቱ የገበያ ዋጋ ጋር ሲነፃፀር የተጋነነ ከሆነ ጨረታው ውድቅ ይሆናል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ጨረታውን ለማዛባት የሞከረ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ሆኖ ወደፊትም በመንግሥት ጨረታ እንዳይሳተፉ ይደረጋል፡፡
- አሸናፊው የተጫረተውን የመኪና እቃና ጎማ ማሸነፉ እንደተገለፀ ውል የመውሰድና ንብረቱን በራሱ በማጓጓዝ ግዥ ፈጻሚ ንብረት ክፍል ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 222 00 12 መደወል ይችላሉ፡፡
የተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት