ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
109

የፍ/ሠላም ሆስፒታል ለ2017  በጀት ዓመት አገልግሎቶችን ለመግዛት ማለትም  ሎት 1. ተኝቶ ታካሚዎች የበሰለ ምግብ አቅርቦት፣ ሎት  2. የጄኔሬተር እና የመኪና ቅባቶች ግዥ እና ሎት 3. የመድሃኒት እና የኦክስጅን ጭነት  ግዥ  ለመፈጸም በዘርፉ ፈቃድ የአላቸው ነጋዴዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት ውል በመያዝ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች  ከዚህ በታች በዝርዝር የቀረቡትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በውድድሩ እንዲሳተፋ ይጋብዛል፡፡

  1. የታደሰና በዘርፋ ሕጋዊ የሆነ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ የግብር ከፋይነት መለያ /ቲን/ ሰርተፊኬት ያላቸው ማቅረብ የሚችሉ እና የምግብ አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና ሚመለከታቸውን ማስረጃዎች የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. የበሰለ ምግብ አቅራቢ ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኝት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 00 /ሃምሳ ብር/ በመክፍል ግዥ ፋይናስ የሥራ ሂደት ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቅናት በየር ላይ የሚውል ሲሆን በተጠቀሰው ቀን ውስጥ  ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
  4. የበሰለ ምግብ አቅርቦት ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር/፣ የጀኔሬተርና የመኪና ቅባት አቅርቦት ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ እና የመድሃኒትና የኦክስጅን ጭነት ተጫራቾች 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. የበሰለ ምግብ አቅርቦት ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ 80,000 /ሰማንያ ሺህ ብር/ የጀኔሬተርና የመኪና ቅባት አቅርቦት ተወዳዳሪዎች 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ የመድሃኒትና የኦክስጅን ጭነት ተጫራቾች 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአማረኛ ቋንቋ ሰርዝ ድልዝ ሳይኖር በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ መሠረት በመሙላት የድርጅቱን ሕጋዊ ማህተም በየገጹ በማድረግ፣ ፊርማና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሆሰፒታሉ ግዥ ፋይናንስ ደጋፊ የሥራ ሂድት ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ጨረታው በአየር ላይ የሚውለው ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ ቀን በአየር ላይ ከዋለ በኋላ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ የጨረታ ሳጥኑ የሚታሸግ ይሆናል፡፡
  8. ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፋይናንስ ቢሮ ክፍል ከቀኑ 3፡30 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያሰተጓጓልም፡፡
  9. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ /ማብራሪያ/ ከፈለጉ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 775 10 16 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡ መሥሪያ ቤቱ  የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመስረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የፍኖተ ሠላም ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here