የምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ለዞን መምሪያ መኪኖች በሎት ግዥ በ2017 በጀት ዓመት ሎት 1. የመኪና መለዋዎጫ እቃ፣ ሎት 2. የመኪና ጎማ እና ሎት 3. የተለያየ አይነት የመኪና ዘይትና ቅባቶች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊውን በመለየት ዓመታዊ ውል በመያዝ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው ከ200,000.00 /ከሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ለሆነ ግዥ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ሎት 1. የመኪና መለዋወጫ (ስፔር ፓርት) ሎት 2. የመኪና ጎማ፣ ሎት 3. የተለያየ አይነት የመኪና ዘይትና ቅባቶች አይነት ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡ የዞኑ አድራሻ ምዕ/ጎንደር ዞን ገ/ውሃ ከተማ ከአቢሲኒያ ባንክ 3ኛ ፎቅ ላይ ይገኛል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደ የታወቁ ባንኮች ሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ መሂ 1 በተቆረጠ በጥሬ ገንዘብ ዋጋ ሁለት በመቶ የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ግዥውን ዋጋ ገቢ በማድረግ ከፖስታው ውስጥ ማስገባት ወይም በተጫራቾች የሚሞላውን የጨረታ ማስከበሪያ ቅፅ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡ የጨረታ ሰነዱን 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ ገዝተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ጨረታውን ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በምዕ/ጎ/ዞን ገንዘብ መምሪያ ግ/ን/አስ/ቡድን መሪ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ14/12/2016 ዓ/ም እስከ 28/12/2016 ዓ/ም ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ መቆያ ጊዜ ዓመታዊ ውል ስለሚሆን የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለተጨማሪ ውል እስኪቋረጥ ድረስ ለሚቆይ 60 ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው በ29/12/2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 በገንዳ ውሃ ከተማ በምዕ/ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግልፅ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በሎት ጥቅል ድምር ስለሆነ የእያንዳንዱ ዝርዝር ዋጋ መሞላት አለበት፣ ካልተሟላ ግን ከጨረታ ውጭ የሚሆን መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ጨረታ ሰነድ ላይ ከተቀመጠው የዋጋ መሙያ ፎርም በስተቀር በማሳሰቢያ የሚሞላ ዋጋ የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ የሚከፈትበት ሰዓት እንደተጠበቀ ሆኖ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 331 08 80/ 058 331 06 32 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊ ድርጅት የውል ማስከበሪያ የሞላውን ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም ሲፒኦ በማስያዝ በምዕ/ጎንደር ዞን/ዐቃቢ ሕግ መምሪያ በመቅረብ ውል መውሰድ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ