የአብክመ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ እና የባህል ቱሪዝም ቢሮ እንዲሁም የቅርስ ጥበቃ ል/ፈ/ጽ/ቤት በአንድ ግቢ ሁለት ህንፃዎች ለቢሮው አገልግሎት የሚውሉ ለ2017 በጀት ዓመታዊ የመኪና የመድን ሽፋን/የኢንሹራንስ ዋስትና፣ የመኪና ጥገና/ጋራዥ/፣ የባነር ህትመት፣ ዓመታዊ መጽሄት፣ ክብ ማህተም፣ የስም እና የስልጣን ቲተር፣ የሠራተኞች መታወቂያ እና የደረት ባጅ እንዲሁም የቢሮው ጽዳት /አውትሶርስ/ አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አውዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200‚000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆንናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ተነባቢና ግልፅ የሆነ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በ100.00/አንድ መቶ ብር/ ከግ/ፋይ/ንብ/አስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 213 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የዕቃው ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /Unconditional Bank Garntee/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሴ/ህ/ማ/ጉ/ቢሮ በግ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ወይም ቢሮ ቁጥር 213 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 15ኛው ቀን ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ክፍል በቢሮ ቁጥር 213 በ16ኛው ቀን በ8፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን በ8፡30 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ባ/ዳር ቀበሌ 16 ግብርና ምርምር ቢሮ ፊትለፊት ካለው ህንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 213 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 0582204270 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 0582265864 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአብክመ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ