የደብረ ማርቆስ አጠቃላይ ስፔሻላዝድ ሆስፒታል በ2017 በጀት ዓመት ለሆስፒታል አገልግሎት የሚውል ሴኪዩሪቲ ካሜራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የንግድ ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ያላቸው፡፡
- በዚህ ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ቫት ተመዝጋቢ ብቻ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ 3,000.00 /ሦስት ሺህ / ብር ብቻ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ኦርጅናሉን ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ የደረሰኞችን ፎቶ ኮፒ ከፋይናንስ ወይም ከዋጋ ማቅረቢያ ፖስታ ውስጥ አስገብቶ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአየር ላይ ለ15 ቀን ቆይቶ በ16 ተኛው ቀን ይከፈታል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ የስብሰባ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡
- የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አ/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን አንስቶ የሚቆጠር ዝቅተኛ ቀን ከ40 ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
- የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለዉጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታዉ ራሳቸዉን ማግለል አይችሉም፡፡
- ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከግ/ፋ/ን/አ/ደ/የስ/ሂደት በአካል በመገኘት/ በስልክ ቁጥር 058 771 22 46 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደብረ ማርቆስ አጠቃላይ ስፔሻላዝድ ሆስፒታል