የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕላንና ልማት ቢሮ ለራሱ ለፕላንና ልማት ቢሮ እንዲሁም በፑል አገልግሎት ለሚሰጣቸው ለትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ባለስልጣን እና ለአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ባለስልጣን የ2017 በጀት ዓመት የኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ ዕቃዎች ሎት 1. የፈርኒቸር ዕቃዎች፣ ሎት 2. የመኪና ጎማ እና ሎት 3. አቅርቦት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ አግባብ ያለው እና የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ከ200.000.00 /ከሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ለሚገዙ ዕቃዎች ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል በአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 223 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ከመጫረቻ ሠነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ (ANRS Plan and Development Bureau) በሚል ስም ተዘጋጅቶ መቅረብ አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የእያንዳንዱን ተቋም በመለየት ለሎት 1. (የኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ ዕቃዎች) ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በተለያየ ፖስታ ማለትም ቴክኒካል የመጫረቻ ሰነዳቸውን በአንድ ፖስታ “ቴክኒካል መመዘኛ” እና ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሌላ ፖስታ” የዋጋ መወዳደሪያ” እንዲሁም ለሎት 2. (የፈርኒቸር ዕቃዎች) እና ለሎት 3. (የመኪና ጎማ) ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዳቸውን ብቻ “የዋጋ መወዳደሪያ” የሚል ጽሑፍ በመጻፍ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች /ሕጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት በአብክመ ኘላንና ልማት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 001 ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ይታሸግና 4፡30 ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ድርጅት የሚመረጠው በእያንዳንዱ ተቋም በነጠላ ዋጋ ዝቅተኛ ያቀረበ ድርጅት ይሆናል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአብክመ ኘላንና ልማት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 001 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 64 27 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ