ለአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ የጽሕፈት መሣሪያ እና የዋይፋይ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ሲያቀርቡ የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሰነድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል አብክመ ፍትህ ቢሮ ከግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለጽሕፈት መሣሪያ ለሚወዳደሩበት 3,000.00 /ሦስት ሺህ ብር/ እና ለዋይፋይ እቃዎች ለሚወዳደሩበት 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በአብክመ ፍትህ ቢሮ ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማለትም ከ 16/07/2016 እስከ 30/07/2016 ዓ.ም ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 04 በ16ኛው ቀን በ01/08/16 ዓ.ም 3፡30 ታሽጐ በ4፡00 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በዚሁ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 31 00 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡