በሰሜን ወሎ ዞን የሸደሆ መቄት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውሉ የህክምና መሳሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃ፣ የጽሕፈት መሳሪያ፣ ደንብ ልስብ፣ የውሃ ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች ሕትመት ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስልሆነም መወዳደር የምትፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በግልጽ /ግዴታዎች/ ማሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡
በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቀረብ የሚችሉ፡፡
የግብር መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
ተጫራቾች ጥራት ያላቸው ዕቃዎች ማቅረብና ባቀረቡት ዕቃ ላይ ጥራት የሌላቸውን ቢያቀርቡ የመቀየር ግዴታ አለባቸው፡፡ የተገዙ እቃዎች የሚገጣጠሙ ከሆነ የመገጣጠምና የመገጣጠሚያን ወጭ በራሳቸው ይሆናል፡፡
የጨረታ ሰነዶች ዋናውንና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
የግዥ መጠኑ ከ200,000.00 (ከሁለት ሁለት ሸህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ አንድ በመቶ ማስያዝ አለባቸው፡፡
የጨረታ አሸናፊው የውል ማስከበሪያ አስር በመቶ ማስያዝ አለባቸው፡፡
አንድ በመቶ ሰነድ ማስከበሪያ አስር በመቶ የውለታ ማስከበሪያ በሆስፒታሉ የውስጥ ገቢ ደረሰኝ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
ጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ሰነዶች መቄት ወረዳ ሸድሆ መቄት የመጀመረያ ደረጃ ሆስፒታል የግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ የሥራ ሂደት ቢሮ የማይመለስ 30.00 /ሰላሳ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
የጨረታ ሰነዱ የሚገባበት ጨረታው ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ ከ2፡30 እስከ 3:30 ይሆና፡፡
የጨረታ ሰነዱ የመከፈተው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሲሆን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
ተጫራቾች በክልሉ የግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1/2003 ተገዥ መሆን አለባቸው፡፡
ሆስፒታሉ በጨረታ ሰነዱ ለተዘረዘሩ እቃዎች ሃያ በመቶ የመቀነስና መጨመር መብት አለው፡፡
ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃ ለማቅረብ ውል በፍትሕ መውሰድ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች ያሸነፋትን ዕቃ መቄት ወረዳ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግቢ ድረስ ዕቃውን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ሆስፒታሉ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የጠበቀ ነው፡፡
አሸናፊዎች ያሸነፋትን ዕቃ ወይም መድሃኒት ቤቱ እንደ ሁኔታው አይቶ በሎት ድምር ወይም በተናጠል አሸናፊ ሊያደርገው ይችላል፡፡
ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው በስልክ ቁጥር 033 211 07 26/ 033 211 00 00 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የሸደሆ መቄት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል