በምሥራቅ ጎጃም ዞን በሞጣ ከተማ አስ/ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ለሞጣ ጤና አጠ/ጣቢያ አገልግሎት የሚውል ሎት 1. ሕትመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሳተም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል፡፡
የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተወዳዳሪዎች በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-3 ድረስ የተዘረዘሩትን የሚመለከታቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሃሳባቸውን በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሞጣ ጤና አጠ/ጣቢያ ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 7 ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት በመጀመሪያ ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር ላይ የሚውል ሲሆን የጨረታ ሰነዱን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት አስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 7 በ16ኛው ቀን 4፡15 ላይ ይከፈታል ቀኑ ቅዳሜና እሁድ /የህዝብ በዓል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
የጨረታ ሠነዱን ቢሮ ቁጥር 7 50.00 (ሃምሳ ብር) የማይመለስ በመክፈል መውሠድ ይችላሉ፡፡
የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ ሰፔስፊኬሽን ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ ለመጠየቅ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 661 00 02 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋውን ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ከፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
መሥሪያ ቤቱ የሚገዙትን እቃዎች ላይ ሃያ በመቶ የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የሚገዙ እቃዎችን አሸናፊው ተቋሙ ድረስ አጓጉዞ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
አሸናፊ የሚለየው በሎቱ ወይም በጠቅላላ ድምር ይሆናል፡፡
የግዥ መጠኑ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ማስያዝ አለባቸው፡፡
የሞጣ ከተማ አስ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት