ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
114

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የጭልጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለተለያዩ መሥሪያ ቤቶች  ቢሮ ለማስገንባት የግንባታ መሳሪያዎችን /እቃዎችን/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፡፡

የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፡፡

የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

የሚገዙ የዕቃዎች ዓይነት ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሸን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡

በጨረታው ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-5 የተጠቀሱትንና የሚፈለግባቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒውን በጀርባው ላይ ከዋናው ጋር ተገናዝቧል ብሎ በመጻፍ ማህተም፣ ስም፣ ፊርማና ቀን በማስቀመጥ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ ቢሮ ቁጥር 7 ከረዳት ገ/ያዥ ድረስ በመምጣት መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ አንድ በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ በመክፈል ደረሰኙን ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም በሲፒኦ ከሆነ በባንክ የተረጋገጠ ሲሆን ሲፒኦው ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡

ማንኛውም ተጫራች የሚጫረቱበት ዋጋ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ በመሙላት አንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ፖስታዎች ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ላይ ስማቸውንና አድራሻቸውን በመጻፍ በጭልጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ከግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን  ቢሮ ቁጥር 1 ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን ፖስታው እስከተገለፀው ቀን ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ በ16ኛው ቀን ጠዋት በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡ ጨረታው ሁሉም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 ውስጥ ይከፈታል፡፡

ተጫራቾች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡

አሸናፊዎች የውል ማስከበሪያ አስር በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ጨረታው ከመከፈቱ በፊት መቅረብ ያለበት ማስተካከያ ካለ ከ10 ቀናት በፊት ማቅረብ ይቻላል፡፡

አሸናፊዎች የሁሉም ምድብ ዕቃዎች የሚያቀርቡት በጭ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በራሳቸው ወጭ ይሆናል፡፡

ተጫራቾች ለውድድር ከቀረቡ በኋላ ሀሳባቸውን መለወጥ/ማሻሻል/ ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡

ለበለጠ መረጃ ከግ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 43 38 46  በመደወል መረጃ  ማግኘት ይችላሉ፡፡

መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ጨረታው ሲሞላ ሥረዝ ድልዝ ካለው ጨረታው ሙሉ በሙሉ ውድቅ ይሆናል፡፡

የጨረታ አሸናፊውን የምንለየው በጥቅል ድምር ወይም በተናጠል ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ፡- የጨረታ ሰነዱ ሲሞላ ሁሉንም አይተሞች መሞላት አለባቸው፤ ክፍት መሆን የለበትም፡፡ በየገፁ የድርጅትዎ ማህተምና ፊርማ ይደረግበት፡፡

የጭልጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here