ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
125

የሰሜን ወሎ ዞን የመርሳ ከተማ አስተዳደር ከ/መ/ል/ጽ/ቤት የሊዝ ጨረታ ኮሜቴ የከተማ ቦታን በሊዝ ሰለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀጽ 1 በፊደል ተራ ቁጥር ከሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት ለኢንቨስትመንት አገልግሎት የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም አካል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከጥቅምት /18/2017 ዓ.ም ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃ ማወቅ እና የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የማይመለስ 600.00 /ስድስት መቶ ብር/ በመክፈል በመሬት ልማትና አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 በመምጣት ዘወትር በሥራ ስዓት መግዛት የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ቦታው የሚገኝበት አድራሻ

ተ.ቁ የጨረታው አይነት የጨረታው ዙር የቦታው መገኛና ቀበሌ የቦታው ስፋት የቦታው አገልግሎት ለቦታው የተሰጠው የጨረታው ኮድ ቁጥር
1 መደበኛ 1ኛ ዙር 02 ቀበሌ ከእቋርአበራ ቤት ጀርባ 212 ካ.ሜ ለኢንቨስትመንት ድርጅት 01
2 መደበኛ 1ኛ ዙር 03 ቀበሌ ከሃብሩ ወረዳ ት/ጽ/ቤት ፊት ለፊት 1700 ካ.ሜ ለኢንቨስትመንት ድርጅት 02
3 መደበኛ 1ኛ ዙር 01 ቀበሌ ከሮዝ ካፊ ፊት ለፊት 313.6 ካ. ለኢንቨስትመንት ድርጅት 03
4 መደበኛ 1ኛ ዙር 02 ቀበሌ ከቡሆሮ ህ/ስራ ማህበር በስከ ሰሜን አቅጣጫ 864 ካ.ሜ ለኢንቨስትመንት ድርጅት 04
5 መደበኛ 1ኛ ዙር 02 ቀበሌ ከቡሆሮ ህ/ስራ ማህበር በስከ ደቡብ አቅጣጫ 935 ካ.ሜ ለኢንቨስትመንት ድርጅት 05

 

የጨረታው ዙር 1ኛ ዙር የ2017 ዓ.ም

የጨረታው ዓይነት፡- መደበኛ

ቦታው ከማንኛውም ክርክር ነፃ ነው

የቦታው ደረጃ 1ኛ

በቦታው የሚፈቀደው አገልግሎት አይነት የህንፃው ከፍተኛ የግንባታ ወለል ግቢ ስፋት ንጽጽር በፕርስንት ሆኖ ቦታው ለሆቴል፣ ለምግብ አዳራሽና ለምኝታ አገልግሎት የሚውል ሲሆን ከፍታውም G+4 ፎቅና ከዚያ በላይ ሆኖ ሰባ በመቶ የቦታው ስፋት በግንባታ ይሸፈናል፡፡

የጨረታው መነሻ የሊዝ ዋጋ ለ1 ካሬ 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ፡፡

የሚፈለገው አነስተኛ የቅድሚያ ክፍያ መጠን አጠቃላይ የቦታውን ዋጋ ሃያ በመቶ ይሆናል፡፡

የቀሪ ክፍያ ማጠናቀቂያ መጀመሪያ ክፍያ ከተከፈለበት ከ2 ዓመት የእፎይታ ጊዜ በኋላ ጀምሮ እሰከ ሊዝ ዘመኑ 40 አመት (አርባ) ይሆናል፡፡

አሸናፊ ተጫራች ማሸነፍ እንደተገለፀለት በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ጊዜ ውስጥ የጨረታውን ዋጋ ከሃያ በመቶ ያላነሰ ቅድሚያ ክፍያ ወይም በቴክኒካል ፕሮፖዛሉ ላይ የገለፀውን ቅድሚያ ክፍያ በመፈፀም ውል ይፈፀማል፡፡ በተጠቀሰው ቀን በሚሰጠው ጊዜ ያልቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል፡፡ 2ተኛ የወጣው አንደኛ የወጣውን ዋጋ በመስጠት መውሰድ ከፈለገ ይሰጠዋል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ የተጫረተበትን ቦታ ስፋት በቦታው የመነሻ ዋጋ በማብዛት የሚገኘውን ውጤት አምስት በመቶ ያላነሰ በኦርጅናል ፖስታ ውስጥ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡

ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናል አንድ ኮፒ በማድረግ በስም በታሸገ ኢንቨሎፕ ታሽጎ በጽሁፍ ለይቶ ማቅረብ አለባቸው፡፡

በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የሚጫረቱበትን የቦታ ዋጋ በፊደልና በአሀዝ መሙላት ይኖርበታል፡፡ በፊደልና በአሀዝ በተፃፈው መካከል ልዩነት ካለ በፌደል የተፃፈው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡

አንድ ተጫራች ለአንድ ቦታ ከአንድ ሰነድ በላይ መግዛት አይቻልም ገዝቶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡

የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚጀምርበት ጊዜ 18/02/2017 ዓ.ም እስከ 29/02/2017 ዓ.ም በአስር የሥራ ቀናት ከቀኑ እስከ አስራ አንድ ስዓት ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡

በሰነድ ማሳሰቢያው ሀሳብ ላይ በፊደልና በአሀዝ የተፃፈው ሥርዝ ድልዝና የሚያምታታ ከሆነ ተቀባይነት የለዉም፡፡

የጨረታው የሰነድ ሽያጭ የሚያልቅበት ጥቅምት 29/2017 ዓ.ም በ11፡00 ይሆናል፡፡

ሰነዱን በመሬት ልማት አስተዳደር ዋና የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 (ሁለት) በመምጣት በሥራ ሰዓት መግዛት ይቻላል፡፡

ቦታውን መጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች በማንኛውም የሥራ ስዓት በአካል በመቅረብ የምናስጎበኝ ይሆናል፡፡

ጨረታው የሚከፈተው ህዳር /02/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡00 በመርሳ ከተማ አስተዳደር ህንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡

ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ወይም ማብራሪያ የሚፈልጉ ከሆነ በሚከተለው ስልክ ቁጥራችን 033 333 00 68 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

መሥሪያ ቤቱ በጨረታው ካልተስማመ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የመርሳ ከተማ አስተዳደር ከ/መ/ል/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here