በሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር የደባርቅ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓ.ም በወረዳው ለሚገኙ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. የጽሕፈት መሳሪያ እና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች፣ ሎት 2. የደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ የተዘጋጁ አልባሳት እና ጫማዎች፣ ሎት 3. የስፖርት ትጥቅ፣ ሎት 4. የመኪና መለዋወጫ እቃ እና ሎት 5. የመኪና ጎማ በግልፅ ጨረታ አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ተጫራቾች ሊያሟሉት የሚገባቸው፡-
በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ የተቀበሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች የሚጫረቱት የግዥ የገንዘብ መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
የሚገዙት የእቃ ዓይነትና ዝርዝር መገለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር / በመክፈል ደባርቅ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ከፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም ሲፒኦ /በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1/ ጨረታው እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ ለግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ውስጥ ወይም ከኦርጅናል ጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ በማሸግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይሁን እንጅ የጨረታ ማስከበሪያ ጥሬ ገንዘብ ፖስታ ውስጥ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አይፈቀድም፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይም ያስያዙት ሲፒኦ (ጥሬ ገንዘብ) ከሁለት በመቶ ቢያንስ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተጫራቾች ከውድድሩ ውጭ ይሆናል፡፡
ማንኛውም ተወዳዳሪ ለሚወዳደሩበት ጨረታ በየሎቱ የጨረታ ማስከበርያ ሁለት በመቶ ነጣጥለው ማቅረብ አለባቸው፡፡
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ሲሞሎ ሥርዝ ድልዝ ካለው በራሳቸው ፊርማ ፓራፍ በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደባርቅ ዙርያ ወረዳ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ስዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
አሸናፊ ድረጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ውል ማስከበርያ አስር በመቶ /በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ በማስያዝ ውል መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ጨረታው በአየር ላይ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ይሆናል፡፡
ይሁን እንጅ የመክፈቻ የመጨረሻ ቀን ጋዜጣው ከወጣበት በ16ኛው ቀን ሆኖ ይህ ቀን በዓል /በካላንደር/ ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የመንግሥት የሥራ ቀን ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 በግልጽ ይከፈታል፡፡
የርክክብ ቦታ ከሎት 4. /ከመኪና መለዋወጫ እቃ/ ውጭ ያሉት እቃዎች ደባርቅ ዙርያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በስሩ በሚገኙ በየፑሉ ንብረት ክፍል ሲሆን ሎት 4. /የመኪና መለዋወጫ እቃ ግን ማእከላዊ ጎንደር ከተማ መኪናዎች በሚጠገኑበት ጊዜ ርክክብ የሚፈፀም ይሆናል፡፡
ተጫራቾች በሚያቀርቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው የጨረታ ውድድር የሚካሄደው በሎት /በድምር/ ዋጋ ይሆናል፡፡
የጨረታ መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና እራሳቻውን ማግለል አይችሉም፡፡
መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
መሥሪያ ቤቱ ከአሸናፊ ድርጅት ውል በሚሰጥበት ጊዜ ከጠቅላላ ዋጋው ሃያ በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብት አለው፡፡
በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈለጉ አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው በሥራ ሂደቱ ቢሮ ቁጥር 3 ዘወትር በሥራ ሰዓት በአካል ቀርበው ወይም በስልክ ቁጥር 058 117 00 11 ወይም 09 18 43 91 36 ወይም በፋክስ ቁጥር 058 117 04 21 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ:- ማንኛውም ተጫራች /ተወዳዳሪ/ የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ ሳምፕል ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ሳምፕል ያስቀመጥን ሲሆን በሳምፕሉ መሰረት ሞልተው በሳምፕሉ መሰረት ገቢ ማድረግ አለብዎት፡፡
የደባርቅ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት