በሰሜን ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የመቄት ወረዳ ፍ/ቤት አገልግሎት የሚውል የጽሕፈት መሳሪያ፣ የፅዳት እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ደንብ ልብስ፣ ቋሚ እቃ እና ህትመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ለውድድር ይጋበዛል፡፡
የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው /የቲን/ ተመዝጋቢ የሆኑ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
የንግድ ፈቃድ እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ በታሸገ ኢንቭሎፕ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ግዥ ፈፃሚው ፍ/ቤት በጨረታ ሰነዱ በተዘረዘሩት እቃዎች ሃያ በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው፡፡
ተጫራቾች ጥራት የሌላቸውን የእቃ አቅርቦት ቢያቀርቡ ፍ/ቤቱ ካቀረበው ስፔስፊኬሽን ውጭ ከሆነ በፍተሻ ተረጋግጦ የተበላሸ እና ፎርጅድ ከሆነ የመቀየር ግዴታ አለባቸው፡፡
የግዥ መጠኑ ከ200,000.00 /ከሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉት እቃ ድምር ዋጋ አንድ በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን ውስጥ የጨረታ ሰነዱን መቄት ወረዳ ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 13 በመምጣት ለእያንዳንዳቸው ሰነድ የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድና ማስገባት ይችላሉ፡፡
የጨረታ ሳጥኑ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ ጨረታው ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እና በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል፡፡
ተጫራቾች የክልሉን የግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1/2003 ተገዥ መሆን አለባቸው፡፡
የጨረታው አሸናፊ በአሸነፈበት እቃ ላይ ውል በፍትህ መውሰድ የሚችልና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ለአንድ ዓመት ጋራንት የሚሰጥ መሆን አለበት፡፡ በተጨማሪም ፍ/ቤቱ ካቀረበው ስፔስፊኬሽን ውጭ ከሆነ በፍተሻ ተረጋግጦ ይመለሳል፡፡
ተጫራቾች ያሸነፏቸውን እቃዎች በሙሉ መቄት ወረዳ ፍ/ቤት ፍላቂት ከተማ አገልግሎት በሚሰጥበት ቢሮ ግቢ ድረስ እቃውን ማምጣት እና በውለታው ቀን ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
ፍ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሆኖ ተጫራቾች ባወጡት ወጭ ፍ/ቤቱ የማይጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
መረጃ ለመጠየቅ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 033 211 00 34 ወይም 033 211 01 28 መቄት ወረዳ ፍ/ቤት ግዥ/ክ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የመቄት ወረዳ ፍ/ቤት