በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ በበላይ ዘለቀ ክፍለ ከተማ ለሃን ጤና ጣቢያ አንድ ብሎክ ለማስገንባት ስላስፈለገ በውስን ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ BC & GC ደረጃ 7 እና በላይ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- የዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- ግብር ከፋይ መለያ (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚሠራው የግንባታ ሥራ ዝርዝር መግለጫ (BOQ) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ ከፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 04 በመክፈል ሰነዱን ማግኘት ይቻላል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሚወዳደሩበት ሥራ 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር / በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ሰነዶችን ለመለየት እንዲቻል በግልጽ ጽሑፍ ኢንቨሎፑ ላይ በመፃፍ ማስታወቂው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ በበላይ ዘለቀ ክፍለ ከተማ ለሃን ጤና ጣቢያ በግዥ/ንብ/አስ/ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 05 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን ክፍል በቢሮ ቁጥር 05 በ16ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በመላክ ወይም በስ.ቁ 058 222 02 37 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡