ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
144

በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን  የጋዞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳችን ላሉ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. የጽሕፈት መሳሪያ፣ ሎት 2. የመኪና ጎማና ባትሪ፣ ሎት 3. የኤልክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 4. የማሽነሪ ኪራይ፣ ሎት 5. የውሃ እቃዎች፣ ሎት 6. ሲሚንቶ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በሎት ድምር ውጤት ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡

የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡

የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን / ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ጋዞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ማግኘት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ዕቃ የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡

ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በጋዞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 16ኛው ቀን 4፡00  ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጋዞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በ16ኛው ቀን 4፡00 ይታሸግና 4፡30 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ጨረታው ይከፈትና በጨረታ ሂደቱ በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡

መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 21 03 22 46/ 09 20 41 56 06/ 09 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የጋዞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here