ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
134

የአብክመ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት አገልግሎት የሚሰጡ ኮድ 04 መለስተኛ ተሽከርካሪ መኪና የጥገና መለዋወጫ እቃ በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡

የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡

የግዥው መጠን 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በኢንስቲትዬቱ ግቢ ቢሮ ቁጥር 19 መግዛት ይችላሉ፡፡

የሚገዙ የዕቃዎችን /አገልግሎቶችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡

ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለፅ ማስታወቂያ በጋዜጣ /ኦንላይን/ ከወጣበት ቀን ከጥቅምት 25/2017 ዓ/ም ጀምሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በኢንስቲትዬቱ የግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 19 ማስገባት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ሎት በጨረታ ሰነዱ የሚገለፀውን የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡

ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በኢንስቲትዬቱ ግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ወይም ቢሮ ቁጥር 19 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጥቅምት 25/2017  እስከ ህዳር 10/2017 ዓ.ም 4፡00  ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

የጨረታ ሳጥኑ ህዳር 10/2017 ዓ.ም 4፡00 ታሽጎ ህዳር 10/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት በስራ አመራር ኢንስቲቲዬት አዳራሽ ይከፈታል፡፡

የመክፈቻው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ስዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

ኢንስቲትዬቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለዉም፡፡

ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ  ቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 23 60 በመደወል ማግኘት ይችላሉ ፡፡

የሥራ አመራር ኢንስቲትዬት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here