በምዕራብ ጐጃም ዞን የዳሞት የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ. ለሰብል ህክምና አገልግሎት የሚውል ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አየር የማያስገባ እና የማያስወጣ የሰብል ማከሚያ ሽራ 28/32 መጠን የሆነ /International standardaized fummigation sheet Air tight/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከፋይናንስ ዋጋ ማቅረቢያ ፖስታ ውስጥ በማስገባት ማስያዝ አለባቸው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ 100.00 /አንድ በመቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከዩኒየኑ ሂሳብ ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በኦርጅናል የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት በድርጅቱ ማህተም በተዘጋጀ ፖስታ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለተከታታይ 11 የሥራ ቀናት እስከ ቀኑ 8፡00 አየር ላይ ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን 8፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በ11ኛው ቀን 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጎልም፡፡
- ጨረታውን ያሽነፈ ተጫራች ጨረታው ተከፈቶ አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ድምር አስር በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ አለበት፡፡ ይህንን ካላደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ሁለት በመቶ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
- ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በዚህ ያልተጠቀሱት ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሠረት የሚሰተናገዱ ይሆናሉ፡፡
- የማስረከቢያ ቦታ ዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየንኃ.የተ ቡሬ ከሚገኘው ጽ/ቤት ድረስ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ተቸማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 774 06 40 በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መስተናገድ ይችላሉ፡፡