ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
109

በአማራ ክልል በደ/ጎንደር ዞን አዲስ ዘመን ከተማ የሚገኘው ርብ ኃላ/የተወሠነ የኅብረት ስራ ማኅበራት ገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒየን ቀበሌ 04 በመደበኛ በጀት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ባለቢዝመንት ሦስተኛ ፎቅ (B+G+3 ፎቅ) ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቹች ለሚቀርቡ ለሲሚንቶ አቅራቢወች በግልፅ ጨረታ በግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ  ይጋብዛል፡፡

አቅራቢወች ህጋዊና የዘመኑን የታደሠ የንግድ  ፈቃድ እንዲሁም ከመንግስት የሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ የተቀበሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ጨረታው ብር 200,000.00/ሁለት መቶ ሺህ ብር/እና በላይ ዋጋ ከሆነ የተጨማሪም እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡

የጨረታ ማስከበሪያ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዛዝ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመጫረቻ ሰነድ በአማርኛ ቋንቋ መዘጋጀት አለበት፡፡

ተጫራቾች በሚሞሉበት የመወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን፣ ፊርማቸው እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡

የጨረታ ሰነዱ በአ/ዘመን ከተማ ብር 500.00/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ለ25 ተከታታይ ቀናት የመጫረቻ ሠነዱን ዋናው ጽ/ቤት ድረስ በመምጣት በአካል/ህጋዊ ወኪላቸው/ በኩል መግዛት ይቻላል፡፡

የጨረታ መዝጊያው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ  ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡

ሲሚንቶው  የሚቅረብበት  አይነትና ቦታ ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡

የመጫረቻ ሰነዱን ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ለ25  ተከታታይ ቀናት ከቀኑ11፡30 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡

የመጫረቻ ሰነዱ በ26ኛው  ቀን ከቀኑ 4፡00  ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30  ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን  በጥንቃቄ   በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀ የጨረታ ሣጥን የጨረታ ማስከበሪያውን ከኦሪጅናል ሰነዱ ፖስታ ወስጥ በማድረግ  ማቅረብ አለባቸው፡፡

ዩኒዬኑ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የሲሚንቶ አቀራርብ ሁኔታ በተመለከተ የተጫራቾችን መመሪያ ይመልከቱ፡፡

አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡

ግልፅ ያልሆኑ ጉዳዬችን በስልክ ቁጥር 0584440061 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ርብ ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ስራ ማኅበራት ገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒዬን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here