በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን አመታዊ የተሸከርካሪዎች ጥገና አገልግሎት የእጅ ዋጋ እና ዋስትናን ጨምሮ እንዲሁም አመታዊ የፎቶ ኮፒ ፕሪንተር እና ፋክስ ማሽን ጥገና አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘረዉን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ተመዝጋቢነት ሰርቲፊኬት ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
የሚገዙ (ዕቃዎች) አገልግሎቶች ዋጋ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
አመታዊ የተሸከርካሪዎች ጥገና አገልግሎት የእጅ ዋጋ እና ዋስትናን ጨምሮ በዘርፉ የታደሰ የሙያ ብቃት ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተገለጹትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከሰነዱ ጋር አብረው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
አመታዊ የተሸከርካሪዎች ጥገና አገልግሎት የእጅ ዋጋ እና ዋስትና ጨምሮ እንዲሁም የፎቶ ኮፒ ፕሪንተር እና ፋክስ ማሽን ጥገና የአገልግሎት ግዥ አይነትና ዝርዝር መግለጫ ጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም ዓይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) አመታዊ የተሸከርካሪዎች ጥገና አገልግሎት የእጅ ዋጋ እና ዋስትና ጨምሮ የአገልግሎት ግዥ 5,000.00 /አምስት ሽህ ብር/ ሲሆን አመታዊ የፎቶ ኮፒ ፕሪንተር እና ፋክስ ማሽን ጥገና አገልግሎት ግዥ 1,000.00 /አንድ ሽህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመስሪያ ቤቱ የገቢ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን እና ደጋፊ ማስረጃቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ አማርኛ መሆን አለበት፡፡
በጨረታው ለመሳተፍ ወይም ለመወዳደር የሚወጡ ወጭዎች ቢኖሩ መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ሁለት አይነት ስለሆነ በሚመለከታችሁ የንግድ ዘርፍ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ተኛው ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 106/107 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ተኛው ተከታታይ ቀን ቆይቶ በ16ተኛው ቀን በ4፡00 ተዘግቶ 4፡30 ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን አዳራሽ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ ህዝባዊ በዓል ወይም ቅዳሜ እሁድ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በራሳቸው ምክንያት ባይገኙ ሰነዱ በሌሉበት ይከፈታል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በተጫራቾች መመሪያ ይዘት ላይ ምንም ዓይነት ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡
የገዥ መ/ቤት አድራሻ አ.ብ.ክ.መ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ባህር ዳር
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ 058 218 00 14 /058 218 11 03 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አብክመ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን
ባ/ዳር