ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
118

የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የጽህፈት መሳሪያ እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃ፣ የፈርኒቸር እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የመኪና ጎማና ዲኮርና ሳኒተሪ እቃዎችን ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታማሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላቸሁ፡፡

  1. በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የታደሠ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ቲን ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና ለእቃው ቀጥተኛ የሆነ የንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
  2. ማንኛውም ተጫራቾች  ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመያዝ ዘወትር በስራ ሰዓት ማለትም ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ ቢሮ ቁጥር 102 ሠነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ በኦርጅናሉ የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት በፖስታ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው፡፡
  4. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከህዳር 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሠነድን በመግዛት በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡15 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በጨረታው ከሚቀርቡ አገልግሎት ከጠቅላላ ዋጋ ላይ  ሁለት በመቶ በባንክ በተመሠከረለት ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ማንኛውም ዋጋ የሚሞላውና ክፍያ የሚፈፀመው በኢትዮጵያ ብር ብቻ ነው፡፡
  1. በጨረታው የሚሳተፈው ተወካይ ከሆነ ህጋዊ የሆነ ውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፤ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
  2. በጨረታዉ አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ ተገልጾለት ውል ከወሰደበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ እቃውን ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  3. በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ቢፈልጉ በስልክ ቁጥር 058 218 14 24 /058 218 06 44 /058 218 00 75 መጠየቅ ይቻላል፡፡
  4. ተጫራቾች ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  5. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here