ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
122

በአብክመ የውኃና ኢነርጅ  ቢሮ በመደበኛ እና በተለያዩ ፕሮጀክቶች የበጀት  ምንጭ ሎት 1. ለደቅ ደሴት የሶላር ኦፍግሪድ(off-grid) ፕሮጀክት የመልሶ ጥገና የዕቃ አቅርቦት ግዥ፣ሎት2. ለቢሮ አገልግሎት የሚውል 40kw የሶላር ፕሮጀክት የዕቃ አቅርቦት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ስለሆነም የሚከተሎትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቶች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. ተጫራቾች ዕቃውን/አገልግሎቶችን ለማቅረብ በዘርፉ(የኤሌክትሮ መካኒካል ዕቃዎች አቅራቢነት) ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ  ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ያላቸው እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቶች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1 እና 2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በውሀና ኢነርጅ በውሃ ተቋማት ግንባታ ግብዓት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 08 ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (እስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ  200.00 /ሁለት መቶ ብር / በመክፈል በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የውሀ እና ኢነርጅ ቢሮ ቁጥር 27 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቶች ለሚያቀርቡት እቃ ለሎት1. 50,000/ሀምሳ ሽህ ብር/  ፣ለሎት2.150,000 /አንድ መቶ ሀምሳ ሽህ ብር/  የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ /ሲፒኦ / ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ህጋዊ ደረሰኝ አሰርተው ማቅረብ  አለባቸው፡፡
  7. የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ከህዳር 30/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 22 ተከታታይ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን የጨረታው መዝጊያ ቀን ደግሞ ታህሳስ 21/2017 ዓ.ም ሲሆን፤ በዚሁ ቀን 4፡00  ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በውሃ ተቋማት ግንባታ ግብአት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 08 4፡30  ላይ ይከፈታል፡፡ የጨረታ መዝጊያ ቀን በዓል ከሆነ በተመሳሳይ ሠዓት በቀጣዩ የስራ ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን የሚያቀርቡት በተሸጠላቸው የጨረታ ሰነድ /ቅጽ/ ብቻ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ሌሎች ተጫራቶች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  10. ቢሮው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
  11. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር +251582-26-24-60/+251 582-20-10-87/+251 582-20-08-55 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአብክመ ውኃና ኢነርጅ  ቢሮ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here