ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
111

ቁጥር 01

በአብክመ የከተሞችና መሰረተ ልማት ቢሮ የቢሮው ፣ የከተሞች ፕላን ኢንስቲትዮት ፣ የምዕራብ ቀጠና አራት ቅ/ጽ/ቤት፣የከተሞች ምግብ ዋስትና እና ሴፍቲኔት ፕሮጀክት እና የUIIDP የ2017 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አላቂ፣ቋሚ እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል ፡፡ ሎት 1. የተለያዩ የፅህፈት መሣሪያዎችና ቋሚ እቃዎች፣ ሎት 2. የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች፣ ሎት 3.ፈርኒቸሮች፣ ሎት 4፡- የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 5.የተለያዩ የመኪና እና የብስክሌት ጎማዎች ከነ ካላማዳሪያው፣ ሎት 6. የመኪና ዲኮር/ ታፒሰሪዎች/ እና ሎት.7 የተለያዩ ህትመቶች በመደበኛ በጀት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅቶች ጋር ውል በመያዝ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን ፡፡

  1. በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. በዘመኑ ግብር የከፋሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብረ ክፍይ መለያ ቁጥር ( ቲን ) ያላቸው፡፡
  4. የግዥው መጠን ብር ከ20ዐ,ዐዐዐ.00 /ሁለት መቶ ሽህ/ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ( ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ከፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚገዙ ዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ከቢሮው ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 27 /28/ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ /ለሚወዳደሩበት ገንዘብ ወይም የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/፤በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በቢሮው ገንዘብ ያዥ ገቢ አድርገው ደረሰኝ ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን አንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በከተሞችና መሰረተ ልማት ቢሮ ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰአት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በከተሞችና መሰረተ ልማት ቢሮ የስባሰባ አዳራሽ በ16ኛው ቀን ይከፈታል፣ቅዳሜ፣እሁድ እና የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን 3:30 ታሽጎ 4:00 ይከፈታል፡፡
  11. ተጫራቾች በሎት 4 የተጠቀሱትን የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ሲሞሉ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ዶክመንት በተለያየ ፖስታ ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቂ በታሸገ ሁለት ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  12. መስሪያ ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 30 ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 50 00 /058 226 61 80/በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡ተጫራቾች ያለምንም ስርዝ ድልዝ የተሞላ ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ሰነዱ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ባጋጣሚ የተሰረዘም ከሆነ የሞላው ድርጅት ፊርማ መኖር አለበት፡፡

በአብክመ የከተሞችና መሰረተ ልማት ቢሮ

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here