ግልፅ  የጨረታ ማስታወቂያ

0
115

ፍሎሬስታ ኢትዮጵያ የአካባቢ መልሶ ማገገም እና ኢኮኖሚ አቅም ግንባታ ፕሮግራም  በአማራ ክልል ፣በደቡብ ጎንደር ዞን በአንዳቤት ወረዳ በርካታ የልማት ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ለፕሮግራሙ አገልግሎት የሚውሉ የልማት መሳሪያ/የጋቢዮን ሳጥን፤ አዷማ፤ አካፋ፤ መዶሻና መናኪሎ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአቅራቢዎች መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅርብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በባህር ዳር ዋና መ/ቤት ድረስ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. የሚገዙ እቃዎች አይነት ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማየት ይችላሉ፡፡ አቅራቢዎች እንደ አስፈላጊነቱ የእቃውን ና ሙና/ሳምፕል/ ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡
  5. አቅራቢዎች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በጥንቃቄ በመሙላት በእያንዳንዱ ገፅ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም በመምታት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በፖስታ ውስጥ አስገብቶ በማሸግ የድርጅታችን ስም በመግለፅ በኢቨሎፕ ላይ በመፃፍ ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ድረስ የእቃወቹን ዋጋ ሞልተው አስፈላጊ ሰነዶች ጋር በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጥዋቱ በ4፡ 00  ላይ ተዘግቶ በዚሁ እለት 4፡30  ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ በ16ኛው
  7. ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
  8. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የቀረበውን የጨረታ ሰነድ መቀየር፤ማሻሻል ወይም ከጨረታው ራስን ማግለል አይቻልም፡፡
  9. የተሰረዘ፤ የተደለዘ፤ የተፋፋቀ ወይም በግልፅ የማይነበብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  10. የጨረታ አሸናፊዎች እቃዎቹን እስከ ዋና መ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  11. ዋና መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታዉን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. አድራሻ፡-ፍሎሬስታ ኢትዮጵያ ዋና መ/ቤት ባሕር ዳር ቀበሌ 13 ትምህርት ቢሮ ጀርባ ነው፡፡

መረጃ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር ፡- 058-220-51-60 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ፍሎሬስታ ኢትዮጵያ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here