በአብክመ የምዕራብ ጎንደር ዞን የአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ገንዘብ/ ጽ/ቤት የግ/ን/አስ/ቡድን መሪ አማካኝነት የ2017 ዓ.ም በመደበኛ በጀት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት1. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት2. የፈርኒቸር እቃዎች፣ ሎት3. የፅህፈት መሳሪያዎች ፣ሎት4. የመኪና ጎማዎች ከነከለማዳሪው ፣ሎት5. አራት ክላስ የሆነ የትምርት ቤት ግንባታ ፣ግድግዳው በእንጨት የሆነ ግንባታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈለጋል፡፡ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፣ የታደስ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸዉ ፡፡
- ግብይቱ ከ200,00 /ከሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባችኋል ፡፡
- ከሁሉም የጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማ መኖር አለበት፤ ስርዝ ድልዝ ካለው በፊርማ መረጋገጥ አለበት የሚያቀርቡት የንግድ ፈቃድና ቲን ግልፅና የሚነበብ መሆን አለበት ፡፡
- በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታችዉን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ስነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ00 /አንድ መቶ ብር/ እያንዳንዱን በደረጃ /በሎት/ተለይቶ የተዘረዘሩትን እቃዎች ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን መግዛት ለሚፈልጉ ተጫራቾች በአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት የግ/ን/አስ/ቡድን አማካኝነት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ከታህሳስ 14/2ዐ17 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 28/2ዐ17 ዓ.ም ለተከታታይ ለ15 ቀናት በአየር ላይ ይውላል ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ /ለሚወዳደሩበት የጨረታ አይነት የዋጋዉን አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /እስፔስፊኬሽን/ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይቻላል ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጆች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሽገ ፓስታ በማቅረብ አዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ገ/ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት እስከ 22ኛው ቀን 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሎት የተዘረዘሩትን ጨረታዎች በ16 ኛው በቀን 9፡30 ታሽጎ በዚሁ ቀን ከ10፡00 ጀምሮ ይከፈታል፤ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ /ወኪሎቻችዉ ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸው እቃዎች ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ በማስያዝ ውል መውሰድና ወደስራ መግባት አለበት ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
- በጨረታዉ መሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአ/አ/ጫ/ወ/ ግ/ን/አስ/ቡድን መሪ ቢሮ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0922718368/0582840410 የሚፈልጉትን ማረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ማሳስቢያ ፡- ከዚህ በፊት በየትኛውም ደረጃ በነበራቸው የአፈፃፀም ችግር ምክንያት የታገዱ ወይም የእቃ አቅርቦት ችግር ያለባቸውን ተጫራቾችን አይጋብዝም፡፡ የፈርኒቸር እቃዎችን ገጣጥሞ ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
የአዳኝ አገር ጫቆ ወረ/ ገን/ ጽ/ ቤት