በአብክመ ፍትህ ቢሮ መ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት እስከ ሰኔ 30/2017 ዓ.ም አመታዊ ተሽከርካሪ ጥገና ጋራዥ፣ አመታዊ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች ፣ የጄኔሬተር ዕቃዎች እና የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዋች ጥገና የእጅ ዋጋ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶችን የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገበ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ.ቁ.1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በታሸገ በፖስታ ማቅረብ አለባቸው ነገር ግን ከላይ ከ1-4 የተጠቀሱትን ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተ/ዳይሬክቶሬት ክፍል ቢሮ ቁጥር 05 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ የዕቃውን ወይም የአገልግሎቱን ዋጋ አመታዊ ተሽከርካሪ ጥገና ጋራዥ 10,00/አስር ሺህ/ ብር አመታዊ የመኪና መለዋወጫ 25,000.00 /ሃያ አምስት ሺህ/ ብር፣ የጄኔሬተር ዕቃዎች 3,000/ሶስት ሺህ ብር/ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዋች ጥገና የእጅ ዋጋ ብር 1,000.00/አንድ ሺህ ብር/በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ/ፖስታ በማድረግ በመ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 04 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት ማለትም ከ 21/04/2ዐ17 ዓ.ም እስከ 5 /05/2ዐ17 ዓ.ም ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ፍትህ ቢሮ መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 በ16ተኛው ቀን በ 6/05/2ዐ17 ዓ.ም በ3፡30 ተዘግቶ በ4፡00 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፣ ነገር ሁሉም ተጫራች ድርጅቶች ከተባለው የመክፈቻ ቀን በፊት ሞልተው ከመለሱ የመክፈቻ ቀኑ ሳይጠበቅ ይከፈታል፡፡
- በሚገዙ የዕቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በመ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582263100/ በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
የአብክመ ፍትህ ቢሮ