በሰሜን ጎጃም ዞን በደ/ አቸ/ ወረዳ ዱርቤቴ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2017 በጀት አመት አጠቃላይ ዓመታዊ ግዥ ማለትም፡ ሎት1. የፅህፈት መሳሪያ፣ ሎት2. የፅዳት ዕቃ፣ ሎት3. የኤሌክትሪክ እቃ፣ ሎት 4.ህትመት፣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፋ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፍይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና ከዛ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና ሌሎች ማስረጃዎችን ጨምሮ ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሠነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ዱርቤቴ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 03 ዘወትር በስራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ ፡፡
- የጨረታ ዝርዝር መረጃ (እስፔስፈኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይቻላል ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ውጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በየምድቡ (በእየሎቱ ) በተለያዩ ፖስታ በማድረግ በጥንቃቄ በማሽግ ደ/አቸ/ወረዳ ዱርቤቴ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 03 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሠዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ማስታወቂያው በጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይቆይና በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ ከጧቱ 4፡30 ህጋዊ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡ በተጨማሪ በጨረታ ሂደቱ በተላለፉት ዉሣኔዎች በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 ተገዥ ይሆናል ፡፡ የመክፈቻዉ ቀን በአል ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 የቅሬታ ቀናት በኃላ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መያዝ ይኖርበታል ፡፡ በተባለዉ ቀን ዉስጥ ውል የማይዝ ከሆነ ግን ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ውርስ ይሆናል ፡፡
- ጨረታዉ የሚካሄደው በየሎቱ ጥቅል ድምር ስለሆነ ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሎት ሁሉንም መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ እንዲሁም የተጠየቀዉን እስፔስፊኬሽን በራሡ መቀየር አይቻልም ፤ስርዝ ድልዝ የበዛበት መሆን የለበትም ፡፡ በስህተት ከተሠረዘ በማያጠራጥር ሁኔታ ፓራፍ ማድረግ አለበት ፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን እቃዎች የማውረጃ እና የማስጫኛ እንዲሁም የትራንስፖርት ወጪውን ችሎ ዱርቤቴ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድረስ ማቅረብና ንብረት ክፍል ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
- የሠነድ መሸጫ ዋጋ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ሠነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- መ/ ቤቱ ባወጣዉ ጨረታ ላይ 20በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነዉ ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ሁሉም ተጫራቾች የግዥ ደንብና መመሪያን ማክበር ይኖርባቸዋል፡፡
- ለበለጠ መረጃ ግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት በአካል ቢሮ ቁጥር 03 ወይም በስልክ 0582230752 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የዱርቤቴ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

