የአብክመ ገቢዎች ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት የጽህፈት መሳሪያዎች ፣ የጽዳት ዕቃዎች እና የተሸከርካሪ ጎማ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳዳር ትችላላችሁ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፍኬት የሚያቀርቡ እና ከ200,000.00 ( ከሁለት መቶ ሺ) ብር እና በላይ ለሚጠይቁ ግዥዎች የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ብር የጽህፈት ማሳሪያዎች 25,000.00/ / ሃያ አምስት ሺ/ ብር ፣ ጽዳት ዕቃዎች ግዥ 10,000.00/ አስር ሺ/ ብር እና የተሽከርካሪ ጎማ 25,000.00/ ሃያ አምስት ሺ/ ብር እና የሚወዳደሩ ከሆነ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተመሰከረለት ቼክ /ሲፒኦ/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀናት በአብክመ ገቢዎች ቢሮ ቁጥር 313 ከላይ ለተዘረዘሩት ግዥ የማይመለስ ብር 150.00 /አንድ መቶ ሀምሳ/ ብር ሰነዱን በመግዛት የነጠላ ዋጋ እና ጥቅል ዋጋ በመሙላት በፖስታ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 313 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ቅዳሜን ጨምሮ እስከ 6፡30 ማስገባት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 313 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም መ/ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብት አለው።
- አስራ ስድስተኛው ቀን ቅዳሜ ፣እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰዉ ሰዓት ይከፈታል።
- የጨረታው አሸናፊ ማንኛውንም ወጭ ራሱ ችሎ ለቢሮው አሸናፊ የሆነባቸውን ዕቃዎች ያስረክባል።
- ቢሮዉ በማንኛውም ሰዓት ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
- አድራሻችን፡- ባህር ዳር ቀበሌ 16 ሜድሮክ ግብርና ምርምር ፊት ለፊት ሲሆን ስልክ ቁጥር 0582265765 ወይም 0582266171 መጠቀም ይቻላል፡፡
የአብክመ ገቢዎች ቢሮ