በደቡብ ጎን/ዞን የሃሙሲት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለሀሙሲት ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በከተማው ውስጥ ለሚያሰራው የኮበልስቶን ንጣፍና የካልበርት ጥገና ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉና ማስረጃ የሚያቀርቡ፡፡
- የግብ ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸዉና ማስረጃ ያላቸው፡
- ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ከብር 200,000/ሁለት መቶ ሽህ/ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡
- የስራ ዝርዝሩ መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር00/ሁለት መቶ/ ብር በመክፈል ከረዳት ገንዘብ ያዥ ክፍል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ለዉድድር ያስቀመጡትን ዋጋ 2 በመቶ ከመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብቻ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ያስያዙትንም ሲፒኦ ወይም የገቢ ደረሰኝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማስገባት አለባቸዉ፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡንና ማስረጃዎችን ዋናዉን በጥንቃቄ በታሸገ በአንድ ፖስታ ለሐሙሲት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን ተብሎ ተጽፎበት ቢሮ ቁጥር 4 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ጨረታዉ በጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ 16ኛዉ ቀን 3፡30 ድረስ ማስገባት ይቻላል ፡፡ የሚታሸገዉም በዚሁ ሰዓት ይሆናል ፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም በገንዘብ ጽ/ቤት በ16ኛዉ ቀን 4፡00 በጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴው ይከፈታል ፡፡
- አሸናፊዉ ማሸነፉ ከተገለጸለት ከ5 ቀናት በኋላ ባሉት 5 የስራ ቀናት ዉስጥ ገንዘብ ጽ/ ቤት ቀርቦ ባሸነፈበት ገንዘብ መጠን ልክ የዉል ማስከበሪያ 10 በመቶ በማስያዝ ዉል መዉሰድ ያለበት ሲሆን በወቅቱ ቀርቦ ዉል ካልወሰደ በግዥ መመሪያዉ መሰረት አስፈላጊዉን እርምጃ ይወሰዳል፡፡
- የስራው ርክክብ የሚፈጸመዉ በባለሙያ ከተረጋገጠ በኋላ በሃሙሲት ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ይሆናል፡፡
- የጨረታ መክፈቻዉ ቀን ቅዳሜ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከናወናል ፡፡
- የጨረታ አሸናፊዉ የሚለየዉ ለሁሉም ስራዎች በሰጠዉ ጥቅል ዋጋ ድምር የሚወስን ሲሆን በሰነዱ ዋጋ መሙያ ቦታ ላይ አንዱንም የስራ ዝርዝር ያልሞላና ስርዝ ድልዝ ያደረገ ተጫራች ከጨረታ ዉጭ ይሆናል ፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ ፡፡
- ስለ ጨረታዉ ዘርዝር መረጃና ማብራሪያ ከፈለጉ ሃሙሲት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0584430320 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ ፡፡
የሃሙሲት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት