ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
104

በደቡብ ጎንደር ዞን በፎገራ ወረዳ አለምበር መሪ መዘጋጃ ቤት ለሚያስገነባው ጠጠር መንገድ ዲችና ካልቨርት ስራ በደረጃ  7 ጠቅላላ ስራ ተቋራጭና በላይ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ የግንባታ ቦታ አለም በር ከተማ ዋና አስፓልቱ እስከ መደሃኒያለም ቤተክርስቲያን ሲሆን፡፡ መወዳደር የሚፈልግ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ግዴታዎች ማሟላት ይጠበቅበታል ፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳዳር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሠ በዘርፋ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆኑን የሚገልፅ ማስረጃ ዋናውንና ፎቶኮፒ ማቅረብ የሚችሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ያላቸው፡፡
  2. የጨረታ መጠኑ ብር 200,000/ ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ30 ተከታታይ ቀናት በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ የሚችሉ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 500 /አምስት መቶ/ ብር በፎገራ ወረዳ አለምበር ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት  በመክፈል መግዛት የሚችሉ ሲሆን የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና ሙሉ አድራሻ በትክክል በመሙላትና በደንብ ፖስታውን በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከተጠየቁት ማስረጃዎች ጋር በማድረግ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  4. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በጽ/ቤታችን ደረሰኝ በጥሬ ገንዘብ ገቢ በማድረግ 150,000 /አንድ መቶ አምሳ ሽህ/ ብር ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ30 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሁኖ ይቆይና 31ኛው ቀን ከጧቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጧቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  5. አሸናፊው ማሸነፉ እንደተገለፀለት የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መውሰድ አለበት ፡፡
  6. ሰነዱን ለሚገዙ ተጫራቾች ዝርዝርና እስፔስፊኬሽን ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ ይቀርባል፡፡
  7. የጨረታ ማስከበሪያ አሸናፊው ድርጅት ውል እንደያዘ ጨረታ ላላሸነፉት አካላት ተመላሽ ይሆናል፡፡
  8. አንድ ተጫራች በሌሎች ዋጋ ላይ ተንርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
  9. አሸናፊው በውሉ መሠረት ከላስረከበ መ/ቤቱ በግዥ መመሪያው መሠረት አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑን መረዳት ይኖርበታል፡፡
  10. በጥቃቅንና አንስተኛ ተደረጅተው ለሚመጡ አካላት ካደራጃቸው ተቋም የድጋፍ ደብዳቤ እና የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  11. አሸናፊው የሚለየው በጥቅል ዋጋ ይሆናል፡፡
  12. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 058 446 14 11 በመደወል መረዳት ይችላሉ፡፡
  13. ጽ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የአለምበር ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here