ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
73

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ አገልግሎት የሚውል የጽዳት እቃዎች እና  የተሸከርካሪ መኪና ዕቃ / የእሪቮ መኪና ኬሪ ቦይ፣የእሪቮ መኪና ፉል ሴት ፣የእሪቮ መኪና ዊንድ ሸድ/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለፅን፡፡ 1ኛ. ሎት 1 የጽዳት እቃዎች ፣ 2ኛ. ሎት 2 የተሸከርካሪ መኪና ዕቃዎች/የእሪቮ መኪና ኬሪ ቦይ፣የእሪቮ መኪና ፉል ሴት፣የእሪቮ መኪና ዊንድ ሸድ/

  1. በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ሰርተፍኬት/የሚያቀርብ፡፡
  3. ከላይ በተ.ቁ 1-2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የሚገዛው ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ / ሺህ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነና የቫት ሰርተፊኬት ኮፒ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩት ለእያንዳንዱ ሎት እቃ ብር 60,000/ስልሳ ሽህ/ብቻ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የሚያስይዙ፡፡
  6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ አብክመ ጤና ቢሮ ግዥ ፋይ/ ንብ/ አስ/ ዳይሬክቶሬት ግዥ ክፍል ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት በ15 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በግዥ ክፍል/ጃይካ ህንፃ ጨረታው በወጣ በ16ኛዉ ቀን በ 8:30 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 9፡00 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በተከታዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል፡፡
  8. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  9. ቢሮው የግዥዉን መጠን እስከ 20 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ለያንዳንዱ ሰነድ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ በመክፈል 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 13 ድረስ በመምጣት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  11. የጨረታዉ አሸናፊ የሆነ ድርጅት ያሸነፈውን የጽዳት እቃዎች እና የመኪና ዕቃ ቢሮ ድረስ አቅርቦና ገጣጥሞ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
  12. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ስለ ጨረታዉ መረጃ ከፈለጉ አብክመ ጤና ቢሮ ቁጥር – ጃይካ ህንፃ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582221127 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡

 

አብክመ ጤና ቢሮ

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here