የዳግማዊ ምኒልክ ጤና ጣቢያ የላብራቶሪ ጣራ ክዳን፣ የህሙማን መቆያ እና ሌሎች ስራዎችንም በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- የዘመኑ ግብር የከፈሉ ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸዉ እና የታተመ ተከታታይ ደረስኝ ቁጥር ያላቸዉ፡፡
- የግዥው መጠን ከ200‚000(ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ከ 10‚000(አስር ሽህ) በላይ ከሆነ 2በመቶ ዊዝ ሆልዲንግ ታክስ ይቆረጥባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ አንድ በመቶ የመጫረቻ ዋጋውን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር በፖስታ አሽጎ በማስገባት ከጨረታ ሳጥኑ ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡
- ተወዳዳሪዎች ደረጃ 7 እና ከዛ በላይ መሆን አለባቸው፡፡
- አርቲሜቲክ ቼክ ከ2.5 በላይ ከሆነ ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡
- ሰነዱ ስርዝ ድልዝ ካለው ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 9 ድረስ በመምጣት በ500 (አምስት መቶ )ብር በመግዛት መውሰድ ትችላላችሁ፡፡
- የመጫረቻ ሰነዱ በፖስታ ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡
- ለመጫረት የሚቀርቡ ማንኛውም ማስረጃዎች ግልፅ፣ በደንብ የሚታይ እና የሚነበብ መሆን አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በምታቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ስማችሁን ፣ ስልክ ቁጥር እና የድርጅቱ ማህተም ሊኖር ይገባል፡፡
- ጨረታው አየር ላይ የሚውልበት ቀን ከ 29/07/2017ዓ.ም ተከታታይ 15 ቀን ሲሆን ፤ጨረታው የሚያበቃው በ14/08/2017 10፡30 ታሽጎ በ15/08/2017 3፡30 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀነዉ ፡፡
የዳግማዊ ምኒልክ ጤና ጣቢያ