በደቡብ ጎንደር ገ/ኢ/ል/መምሪያ የታ/ጋ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በስሩ አገልግሎት ለሚሰጣቸው በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል በመደበኛ በጀት 1. ማሽነሪ ኪራይ/ዶዘር/ ኤፍራታ ቀበሌ 15 የመንገድ ሥራ አገልግሎት የሚውል 2ኛ. የህትመት ውጤቶች 3ኛ. በGCF በጀት የኮንስትራክሽን /ህንጻ/ማተሪያሎች 4ኛ. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች አቅርቦት ግዥ እንዲፈጸምላቸው በጠየቁት መሠረት ከተጫራቾች መካከል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስቀረብ ይፈልጋል:: ስለዚህ ተጫራቾች፡-
- የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው::
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ያላቸው::
- የሞሉት ዋጋ ከ200.000.00/ከሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /የቫት/ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የአቅርቦት ዓይነቶች ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የግንባታ ዓይነት ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና /በመሂ 1 በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው:: ይህም ገንዘብ አሸናፊ ከሆኑ ከውል ማስከበሪያ ጋር ተጨምሮ የሚታሰብ ይሆናል:: ተሸናፊ ከሆኑ ደግሞ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል::
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳብ በአንድ ወጥ በሆኑ ፖስታዎች የድርጅቱን ክብ ማህተም በመምታትና በጥንቃቄ በማሸግ ጽሕፈት እና መሳሪያ ታ/ጋ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በሚቆይ የአቅርቦት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡00 ላይ ይዘጋል:: በዚሁ ቀን 4፡30 ላይ ይከፈታል:: ሆኖም ግን ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኙም ጨረታውን መክፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታ ሂደቱ ለሚተላለፍ ውሳኔዎች ተገዥ ይሆናሉ::
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- አሸናፊው የሚለየው በጠቅላላ ድምር ውጤት /በሎት/ በመሆኑ የተጠየቁትን ዝርዝር አካተው መሙላት አለባቸው::
- መሥሪያ ቤቱ 20 በመቶ የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ታ/ጋ/ወ/ግ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 268 02 18 በመደወል ማግኘት ይችላሉ::
የታች ጋይንት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት