በአብክመ የሴቶች ህፃናትና ማ/ጉ/ቢሮ ለ2017 ዓ.ም በመደበኛ በጀት የተለያዩ ግዥ ፈርኒቸር፣ የመስኮት መጋረጃ፣ የወለል ምንጣፍ ፣የውሃ ታንከር እና የስፖንጅ ፍራሽ/ ለቤተ ህፃናት አዲስ ለተገነባው ህንፃ አገልግሎት የሚውል በግልፅ ጨረታ አውዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- ግዥው መጠን ብር 200000/ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆንናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በዘርፋ የተሰማሩ መሆናቸውን የሚያሳይ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ለእያንዳንዱ ሰነድ ፖስታ ኦርጅናል ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ በነፃ ዋጋ ላይ የተመሰረተ ሆኖ የጨረታ ሰነዱን 00 ብር ከግ /ፋይ /ንብ/ አስ/ ክፍል ቢሮ ቁጥር 213 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ለ 90 ቀናት ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱ ሲያስገቡ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሴ/ህ/ማ/ጉ/ቢሮ በግ/ ፋይ/ ንብ/ አስ/ ዳይሬክቶሬት ወይም ቢሮ ቁጥር 213 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰአት እስከ 16ኛው ቀን በ8፡00 ድረስ ማስገባት አለባችሁ ፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋይ/ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት ክፍል በቢሮ ቁጥር 213 በ16ኛው ቀን በ8፡00 ታሽጎ በእቱ በ8፡30 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ሙሉ በሙሉ ማንበብና ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 213 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 0583209704 በስራ ሰዓት በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአብክመ የሴቶች ህፃናትና ማ /ጉ/ ቢሮ